Sunday, 27 December 2015

ከሁከቱ ምን አተረፍን ?




ዮናስ
መነሻውን የአዲስ አበባባና በዙሪያዋ የሚገኙ ከተሞችን የተቀናጀ ፕላን በማድረግ በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች በተማሪዎች የተጀመረው ተቃውሞ በተወሰኑ አካባቢዎች መልኩን እየቀየረ ወደ ሁከት በመምራቱ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ታዲያ ስለሃገራችን ጸጥታ ደንታ የሌላቸውና ይልቁንም አበረታች እንደሆኑ የሚታወቁቱ ሁሉ የመግለጫ ጋጋታውን ተያይዘውታል፡፡


መንግሥት በኦሮሚያ የተነሳውን መጠነ ሰፊ ተቃውሞ ለማርገብ ያልተመጣጠነ ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠብ በማለት ያሳሰበውና የለመድነው ደግሞ አምነስቲ የተሰኘው ነው፡፡
አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስ ዎች ሰሞኑን በጉዳዩ ላይ ባወጡት መግለጫ፤ መንግስት ተቃውሞ በሚያሰሙ አካላት ላይ ያልተመጣጠነ ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠብ ጠይቀዋል፡፡ መንግሥት የዜጎችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅና ሰላማዊ ተቃውሞ የማድረግ መብት ከማክበር ይልቅ ጉዳዩን ከሽብርተኝነት ጋር ማያያዙ አግባብ አይደለም ብሏል አምነስቲ፡፡ የነዚሁ ድርጅቶች አጃቢ እና አራጋቢው መድረክ ደግሞ እንዲህ አለ፡፡
ተቃውሞውን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት 32 ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ያስታወቀ ሲሆን አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሟቾች ቁጥር ወደ 40 እንደሚጠጋ ገልጿል። የሙሾው ተቀባይ ደግሞመንግሥት ተቃውሞ ያሰሙትን ሁሉ በሽብርተኝነት ፈርጇል ከህግ አግባብ ውጪ በፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀምን ግድያ ከማውገዝ ይልቅ ተቃዋሚዎቹን ሽብርተኛና ሀገር ሊበጠብጡ የተነሱ ናቸው ማለቱ አግባብ አይደለም ሲል ተቃውሟል። የውዝግቡ መነሻ ከሆነው ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ 2006 . ተመሳሳይ ግጭት ተፈጥሮ የበርካቶች ህይወት ጠፍቶ እንደነበር ያስታወሰው ሂውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ፤ ያኔም ሆነ አሁን በተነሳው ተቃውሞ በርካቶች መገደላቸውን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ መታሰራቸውን አስታውቋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በተነሳው ተቃውሞ አብዛኞቹ የተቃውሞው ተሳታፊዎች ተቃውሞ ስላቀረቡ ብቻ ጉዳዩ ከሽብር ተቆጥሮ በሽብር እንደተፈረደባቸው የጠቀሰው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ በወቅቱ ታስረው የነበሩ ተማሪዎች በእስር ቤት ውስጥ ግርፋትና ስቃይ ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡ ከሦስት ሳምንታት በላይ ለዘለቀው ተቃውሞ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎቹ ከመጠን በላይ ኃይል እንዳይጠቀሙ ሊከላከል ይገባ ነበር ያለው "የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ" ህግ የጣሱ አካላት በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለባቸው ብሏል፡፡

አሁን ጉዳያችን የተቃውሞውን ጀርባ ማየትና እንዳተረፈና ከሰረ ማጠየቅ ነው።ቅሬታዎችን ማቅረብ፣ ተቃውሞን በሰላም መግለፅ፣ ተፈጥሯዊ መብት ነው ይላል
ከላይ በተመለከተው አግባብ እነ አምነስቲና መድረክ ያሉት እውነት እንኳ ቢሆን መንግስት፣ ሰላማዊ ተቃውሞን ለማስተናገድ ጨርሶ የማይፈልግ ቢሆንም እንኳ፣ በዚህም ሃላፊነቱን ባለመወጣት ዋና ተጠያቂ ቢሆንም እንኳ፣ እኛስ በራሳችን አቅም፣ ሰላማዊ ተቃውሞ ወደ ብጥብጥ እንዳያመራ መከላከል ስለምን አንችልም? ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው።
መቼም፣ አብዛኛው ሰው፣ ጨዋ ነው። የተቃውሞ ድምፅ ለማሰማትና አቤቱታ ለማቅረብ፣ ወደ አደባባይ የሚወጡ ብዙዎቹ ሰዎችም፣ በአመዛኙ የሰውን ሕይወትና ንብረት ለመጉዳት አይፈልጉም። ታዲያ፣ ለምንድነው በየጊዜው፣ እንዲህ አይነት ቀውስ የሚፈጠረው? እዚህ ላይ ችግር አለ። አብዛኞቹ ሰዎች ጨዋ ቢሆኑም፣ የሰውን ሕይወትና ንብረት ለመንካት ፍላጎት ባይኖራቸውም፤ በሰላማዊ ተቃውሞ መሃል፤ ዝርፊያንና ጥቃትን ለማስቆም ይቸገራሉ። በሌላ አነጋገር፤ መዝረፍና ማቃጠል ለሚፈልግ ሰውጥሩአጋጣሚ ይሆንለታል። ከዚያም አልፎ ራሱን፤ዋና የነፃነት ታጋይ፣ ዋና ተቆርቋሪ፣ ዋና ተወካይአስመስሎ ስለሚሾም፣ተው የሰው ንብረት አትዝረፍ፣ አታቃጥልብለን በድፍረት አንጋፈጠውም። እንዲያውም፣ አለቃ ወይም መሪ ይሆንብናል።እስቲ ተቃውሞውን በመተገን ከሰሞኑ የሆነውን ተመልክተን ማን እንዳተረፈና የመንግስትን እርምጃና የነ አምነስቲን ውግዘት ሂሳብ እናስላ።
ሁከቱ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች/ 9 ዞኖች ውስጥ/ የተከሰተ ቢሆንም በይበልጥም በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሽዋ አካባቢዎች ባሉ የኦሮሚያ ከተሞች ጠንከር ብሎ መታየቱ አይካድም መቼም።
የተፈጠረውን ሁከት አንዳንድ የጠባብና የትምክህት ኃይሎች ለራሳቸው ዓላማ ማራመጃነት ለመጠቀም መሞከራቸው እየታየ እንደሆነና ይህን ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ ወስደው በምርጫ ያጡትን የመንግሥት ሥልጣን ለማግኘት የሚረዳቸውን መንገድ እንደሚፈጥርላቸው በማሰብ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውና አንዳንዶችም ይህን ህልማቸውን የሚያመለክት መግለጫ እያወጡ መሆናቸው፣ ከዚህም ባለፈ የአደባባይ ሰልፍ ለማድረግ እንደተዘጋጁ እየገለጹ መሆኑም እንዲሁ።
የተፈጠረው ሁከት የጸጥታ አስከባሪ ኃይሎችን ጨምሮ በሌሎች ሰዎች ሕይዎት፣ በመንግሥትና በግለሰቦች ንብረት ላይ ጉዳት ያስከተለ መሆኑንም ሙሾ አውራጆቹ ሊያስተባብሉት አይቻላቸውም
በአንዳንድ አካባቢዎች የተነሳው ሁከት ብሔርንና ኃይማኖትን በመለየት በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትና ጉዳት አስከትሎ የነበረ መሆኑ ደግሞ አስከፊው ኪሳራ ነው።
በአንዳንድ አካባቢዎች አመጹ በጦር መሳሪያ ጭምር ተደግፎ ሲካሄድ የነበረ መሆኑንስ ማን ይረሳል።
በአንዳንድ አካባቢዎችም ሁከት ቀስቃሽ ጸረ ሰላም ኃይሎችን በመኪና ጭምር ከአንዱ ስፍራ ወደ ሌላው በማጓጓዝና በማዘዋወር አመጹን የማስፋፋት ሥራ ሲሰሩ የነበረ መሆኑነረም በአደባባይ አይተናል
በአማራ ክልል በመተማና አርማጭሆ አካባቢዎች ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በአማራና በቅማንት ተወላጆች መካከል በጸረ ሰላም ኃይሎች ቀስቃሽነት ግጭት መከሰቱም ሰሞንኛ ክስተት የመሆኑን ግጥምጥሞሽም በለጺካ መነጽር መመልከት ተገቢነት ይኖረዋል።
የቅማንት የማንነት ጥያቄ በክልሉ መንግሥት ቀደም ብሎ ምላሽ የተሰጠው ቢሆንም ጸረ ሰላም ኃይሎች በሕዝቡ መካከል በመግባት ሁከት እንዲነሳ ማድረጋቸውና በዚህም ሳቢያ በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያስከተለ ግጭት መሆኑን መጠራጠር አይገባም።
በዚህ አካባቢ ግንቦት ሰባትን የመሰሉ ጸረ ሰላም ኃይሎች ሰርገው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን አይተናልና፣
ከሱዳን ጋር ካለው የድንበር ማካለል አለ በማለት በፀረ-ሰላም ኃይሎች የሚደረግ ፕሮፓጋንዳ መኖሩ ጋር ተያይዞ የሚደመጥ የተቃውሞ ድምጽ እንዳለ መኖሩም በተመሳሳይ፣
በኦሮሚያ ክልል ከማስተር ፕላኑ ጋር ተያይዞ የተነሳው ተቃውሞ በብዙ አካባቢዎች መልኩን ለውጦ ወደ ለየለት ሁከት ለመቀየር ጥረት መደረጉ፣ ማስተር ፕላኑን ከመቃወም ጋር ተያያዥነት የሌለው የጸረ ሰላም ኃይሎችን ድብቅ አጀንዳ ከበስተጀርባው የያዘ መሆኑ፣ ህገ- መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል የመናድ ሙከራ መኖሩን የሚያረጋግጥ እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይቻልም።
በአገራችን ብቻ ሳይሆን፤ ደረጃው ቢለያይም፣ በሁሉም አገራት፣ የዘመናችን ሦስቱ ዋነኛ አለማቀፍ የቀውስ ምንጮችን ተመልከቱ ሲለን አዲስ አድማስ ሰሞንኛ በነበረው ህትመቱ ያስነበበን ማን እንደከሰረና እንዴት እንደከሰርን የሚያሳየን ሁነኛ ማጠየቂያ ነው።
በመንግስት እልፍ ቁጥጥሮችና ጫናዎች ሳቢያ የሚፈጠርየቅይጥ ኢኮኖሚ ቀውስ በአለም ዙሪያ፣ ከድሃ እስከ ሃብታም አገራት፤ ሁሉንም እያናወጠ አይደል? ግን፤ ጥፋተኞቹ መንግስታት ብቻ አይደሉም፡፡ እኛም እንተባበራቸዋለን፡፡
በአንድ በኩል፤... የግል ኢንቨስትመንትንና ቢዝነስን፣ የግል ስኬትንና ብልፅግናን፣ በአድናቆትና በአርአያነት ለማየት የሚቸገር ኋላቀር ባህል በአገራችን ሞልቷል። በሌላ በኩል ደግሞ፤... በዚህም በዚያም በአየር ባየር አልያም በሙስና፣ በድጐማም ሆነ በልዩ ድጋፍ ... (ያለ ስራ እና ያለ ጥረት) ሃብት ለማግኘትና ተጠቃሚ ለመሆን መዋከብም የተለመደ ነው፡፡
እነዚህ አዝማሚያዎች፤ በብዙ ዜጐች ዘንድ የሚታዩ ስህተቶች ናቸው፡፡ የመንግስት ምላሽስ? መንግስት፤ ቢዝነስን የሚያናንቅን ባህል ለመግታትና የአየርባየር ወከባን ለማስተካከል ከመጣር ይልቅ ወደ ነፃ ገበያ ስርዓት ለመጓዝ ከመትጋት ይልቅ፤ በዚሁ ሰበብ፤ ከነአካቴው ቢዝነስንና ነፃ ገበያን በእንጭጩ የሚቀጭ፣ የዋጋ ቁጥጥርና የዋጋ ተመን፣ የገደብና የክልከላ፣ የታክስ ጫናና የመዋጮ ዘመቻ ማካሄድ ቀላል ይሆንለታል። ያው፤ ቢዝነስ ሳይስፋፋ ደግሞ፣ ከስራ አጥነትና ከድህነት መላቀቅ አይቻልም። አሳዛኙ ነገር፤ በስራ አጥነትና በድህነት እየተማረርን፣ ለዚህ ችግር መፍትሄ እንዲፈለግለትድማፃችንን ለማሰማትአደባባይ ብንወጣ፤ ከሁሉም በላይ ጎልቶ የሚወጣው ድምፅ፣የሸቀጦች የዋጋ ቁጥጥር ይደረግ”... የሚል መፈክር ይሆናል።
ሁለተኛና ሦስተኛ የቀውስ ምንጮች፤ የሃይማኖት አክራሪነትና የዘረኝነት አባዜዎች ናቸው፡፡
አሳዛኙ ነገር፤ እኛም፣ እንመቻችላቸዋለን። የተቃውሞ ድምፅን ለማድመቅ የሚጠቅም እየመሰለን፣ ወይም ደግሞ የተቃውሞ ድምፅ እንዳይደበዝዝ በመስጋት፣... በፅናትና በትጋት ትክክለኛ መላ ከማበጀት ይልቅ፤ ሃይማኖትንና ተወላጅነትን ከፖለቲካ ጋር የማደበላለቅ አዝማሚያ፣ አቋራጭ መፍትሄ ሆኖ ይታየናል፡፡ ወይምጊዜያዊ ችግር ነውብለን በቸልታ እንቀበለዋለን። በዚሁ አዝማሚያ ለመንሸራተት፣ አእምሯችን ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ፤ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን... አክራሪነትንና ዘረኝነትን የሚያስተጋቡ መጥፎ ሰዎችን በዝምታ ለማለፍ፣ ወይም እንደ ጊዜያዊ ችግር አይተን ቸል ለማለት ይዳዳናል። ነገር ግን፣ አንድ ሁለት ሰው የሚያስተጋባው የዘረኝነት ወይም የአክራሪነት መርዝ፣ ከጎናችን ተሰልፎ በዝምታ ስናልፈው፤... ለአፍታ በአዳማቂነት አገልግሎ፣ በራሱ ጊዜ የሚከስም፣ ተራ ችግር አይሆንልንም።
በተገላቢጦሽ፣ ዋና ጉዳያችንን ሁሉ ጠቅልሎ እየዋጠና እየቀበረ፣ ከመክሰም ይልቅ እየተግለበለበና እየተቀጣጠለ ለመስፋፋት እድል ያገኛል፡፡ ብዙም ሳይቆዩ፤ በሃይማኖት
ተከታይነት ወይም በዘር ወደ ማቧደን ይሸጋገራሉ፤ ከዚያም በየፊናቸው የየቡዱኑ አለቃ፣... አድራጊ ፈጣሪ ይሆኑብናል።
እንዲህ፣ ነገር እየተበላሸ፣ አገሬው ወደ መናወጥ እያመራ፤ ብዙዎቻችንየባሰ መጣብለን መስጋት ስንጀምር፤ መንግስት ምን ያደርጋል?
የአክራሪነትን ሽብር፣ የዘረኝነትን ግጭት እየተከላከለ፤ የዜጎችን ቅሬታና ሰላማዊ ተቃውሞ ለማስተናገድ፤ እንዲሁም... የዜጎችን ነፃነትና መብት ለማስከበር መትጋትና መጣር ይችላል። ግን፤ ይሄ አድካሚ ነው። ያው፤ በበርካታ አገራት እንደታየው፤ የዜጎች የተቃውሞ ድምፅ፣ በአክራሪዎች ወይም በዘረኞች ድምፅ እየተዋጠ፣ ነገሩ ሁሉ ይቃወሳል። ብዙ ሰዎች በስጋት ይጨነቃሉ።
በሃገራችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተወገደውን የደርግ ሥርዓት ተከትሎ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚደረገው ርብርብ በየደረጃው የቀጠለ ቢሆንም፤ የዴሞክራሲ ተቋሟት የሚባሉቱ ድርጅቶችም ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና ለመልካም አስተዳደር መረጋገጥ ከእለት እለት እየተጠናከሩና የበለጠውኑ እየሠሩ ያሉበት ሁኔታ ቢኖርም፤ በሃገራችን የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሚዲያው በተለይም ግርግር በተነሳ ቁጥር የተለመደና ጸረ
ዴሞክራሢያዊ የሆነ አካሄዳቸውን ለማለዘብና ወደትክክለኛውና ለሃገራችን እድገት ወደሚጠቅመው መሥመር መመለሥ አለመቻላቸው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው ላይ ከባድ የተባለ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳረፈ ነው፡፡
በአጠቃላይ በዳበረ የዴሞከራሲ ስርዓት ገዥ የነበረ ፓርቲ ተቃዋሚ ተቃዋሚ የነበረውም ገዢ የመሆኑ ጉዳይ የተለመደና የሚጠበቅ ጉዳይ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት የስልጣን ሽግግር ያለአንዳች ችግርና ቀውስ በሰላማዊ መንገድ የሚፈፅም ከመሆኑም ባሻገር ህብረተሰቡ በሚመራባቸው መሰረታዊ አቅጣጫዎች ላይ ይህ ነው የሚባል ለውጥን የሚያስከትል አይሆንም፡፡
ይህ የሚሆነው ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ታማኝ ተቃዋሚ(ሎያል ኦፖዝሸን) በሚል ስያሜ የሚታወቁ የራሳቸው የተለየ ፓሊሲ ከማቅረብ ባሻገር ስርዓቱን የመናድ ሃሳብና ተግባር የሌላቸው ሆነው ሲገኙ ነው፡፡
እንደነ / መራራ ጉዲና በህግ የሚመሩትንና ህገመንግሥታዊ ስርዓቱን አክብረው በተፈቀደው ሜዳ ላይ ለመጫወት ፈቃደኛ የሆኑትንቅልብና ተለጣፊእያሉ አመፀኞችንና ህግና ህገወጥነተን ቀላቅለው የሚጠቀሙትን "ህዝባዊና ሃገራዊ" እያሉ በማሸማቀቅና በማሞገሥ አይሆንም፡፡
በአገራችን ከላይ የተጠቀሰውን አወንታዊ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ጠንካራ ፓርቲዎች እንዳይፈጠሩ እንቅፋት የሚሆኑ ከኋላቀርነታችን ጋር የተያያዙቱ በርካታ ችግሮች እንደተጠበቁ ሆነው በምርጫ ዋዜማ ላይ ብቻ ብቅ ብለው የሚጠፉ የመስቀል ወፍ ፓርቲዎች በሚሰጡት አፍራሽ መግለጫና አራጋቢ ጋዜጦችም አሉታዊ ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑ እየታየ ነው፡፡
ተቃዋሚ መሆን ማለት መናድ ማፍረስ፣ በተገኘው አጋጣሚና ባመቸ ስልት በመጠቀም ማደናቀፍ ተደርጎ የሚወሰድበት ሁኔታ እንዲፈጠር እነዚህ ሃይሎች አሁንም እየሰሩ ስለመሆናቸው ከመግቢያው ጀምሮ ባየናቸው ሁነቶች ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
በጥቅሉ ጉዳዩን ስንፈትውና ስናሰላው የተነሱ ጥቄዎች የመልካም አስተዳደር ችግር የፈጠራቸው ናቸው። የቀረቡትም በፌዴራል ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ ነው።
በኦሮሚያ አካባቢየአዲስ አበባና ኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የኦሮሞ ገበሬዎችን መበተና ጥቅም ይጎላልየሚል ጥያቄ ተነስቷል። በፌዴራል ስርዓቱ ውስጥ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች ከአዲስ አበባ ስለሚያገኙት ጥቅም በህገ መንግስቱ የተቀመጠው መብት ሊሸራረፍ ይችላል ከሚል የቀረበ የመረጃ ጥያቄ ነው።
ህገመንግስታዊ ስርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት ህጋዊ በሆነ ዴሞክራሲያዊ አግባብ ሊቀርቡ የሚችሉና ምላሽም የሚያስፈልጋቸው ነበሩ።

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ከቅማንት ህዝብ ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄም በተመሳሳይ የፌዴራል ስርዓቱ የሚፈቅደው የማንነት ጥያቄ ነው። የክልሉ መንግስት ለተነሳው የማንነት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ሰጥቷል። ይህን ተከትሎ የተነሳው የአስተዳደራዊ ወሰን መለየት ጉዳይም በውይይት ሊጠናቀቅ የሚችልና የሚጠበቅ ጥያቄ ነው።
እነኚህ ጥያቄዎች በወቅቱ መረጃና ወቅታዊ ምላሽ ከመስጠት ጋር በተያያዘ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር የመነጩ ናቸው።
በዋናነት ግን ይህ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የተጀመረው ዘመቻ ከውስጥ ጀምሮ ያለውን የአፈጻጸም ችግር በማስተካከልና የጸረልማት ኃይሎችን መሰረት የሚያሳጣ እንደሆነ ግልጽ በመሆኑ ግርታ ቢፈጥር እንኳ ህይወትና ንብረት የሚያጠፋ ሁከት ለመፍጠር የሚያስችል ምንም መነሻ ግን አልነበረውም።
ፕላኑ ከዚህ በፊት ጥያቄ ቀርቦበት ከህዝብ ጋር ውይይት እስኪካሄድ ድረስ በረቂቅነት ደረጃ እንዳለ የቆመ ነው። ከአተገባበር ጋር ተያይዞ አሁን የተጀመረ ነገር የለም። በሌላ በኩል ህገመንግስታዊ ምላሽ ያገኘው የቅማንት ህዝብ አስተዳደራዊ ወሰንም ሁከት ለማስነሳት የሚያስችል መሰረት የለውም።
መንግስት በዓይነቱና በዝግጅቱ ሰፊ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር መፍቻ ዘመቻ ጀምሯል። ይህ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመንግስት አደራ ያለውና ገዥ ፓርቲውም በጉባኤው ሳይቀር ሊፈታው ቃል የገባበት እና በሰፋፊና በተዘረዘረ ዕቅድ የተጀመረ ተግባር ነው፡፡ የተጀመረው ዘመቻ ለመልካም አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ምክንያት የሆኑ የኪራይ ሰብሳቢነትና ፀረ ልማት ተግባራትን በህዝብ ተሳትፎ የሚበጣጥስ ነው። በዚህ ሂደት በመንግስት መዋቅርና በህዝቡ ውስጥ የተደበቁ ኪራይ ሰብሳቢዎች የሚጋለጡበት ዘመቻ ነው። በአንጻሩ ደግሞ መንግስትና ህዝብ የበለጠ ትስስር እየፈጠሩ በጋራ የሚሰሩበት ዕቅድ ነው፡፡
ይህን ተከትሎም ኪራይ ሰብሰሳቢውና ጸረ ልማት የሆነው ኃይል ከየቦታው ተጠራቶ በመተሳሰር የህዝቡን ትክክለኛ ጣያቄ በማዛባት ብጥብጥና ሁከት ፈጥሯል፡፡
9
የአክራሪነት፣ የጥበት፣ የትምክህትና የሙስና መፈልፈያ የሆነው የመልካም አስተዳደር ችግር ከስር መሰረቱ መፍታት የማይታለፍና ለነገ የማይባል ተግባር ነው፡፡ ህዝብን ከህዝብ ነፃ ማውጣት ማለት ደግሞ የአክራሪነት፣ የጥበትና የትምክህት ምሽግ መናድ ማለት ነው፡፡ የፌዴራል ስርዓቱ በህዝቦች ተሳፎና ተጠቃሚነት የበለጠ እንዲጎለብት ማድረግ ማለት ነው፡፡ በሃይማኖትና በብሔር ስም ህዝብን እያወናበዱ ኪራይ የሚሰበስቡ ጥገኞች ይህን ዘመቻ የፈሩት የጥቅማቸው መሠረት ስለሚናድ እና የፌዴራል ስርዓቱ ጥንካሬ በየጊዜው የሚያደናግሩበትን መንገድ ስለሚዘጋባቸው ነው፡፡
በሁለቱ ክልሎች አንዳንድ አካባቢ ህዝቡ ያነሳው ጥያቄ ህገመንግስታዊና ምላሽ ሊሰጠው የሚችል ነበር። ጥያቄዎቹ የመልካም አስተዳደር ዕቅድን በማቀጣጠል ከስር መሰረቱ የሚመልስ ነበር፡፡
የጥያቄው አቀራረብ በፍጥነት ወደ ሁከት መቀየሩ የፀረ መልካም አስተዳደር ትግሉ መጀመር ያሳሰባቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች አጀንዳውን ለማስቀየር ባደረጉት ጥረት የተፈጠረ ነው፡፡ ጥያቄውን ያነሳው ህዝብ ጥያቄ ያነሳበት ችግር የሚቀረፈውም የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፊያ ንቅናቄውን አጠናክሮ በመቀጠል ነው።
የተማሪውንና የህዝቡን ሠላማዊ ጥያቄ ወደ ሁከት የቀየሩ ወገኖች የየአካባቢውን ንብረትና አቅም በማስገደድና በማደናገር ለመጠቀም ሞክረዋል፡፡ የህዝብ የአስተዳደር ተቋማትን አውድመዋል። ነፍሰጡር የጫኑ አምቡላንሶችን ሰባብረዋል፣ /ቤቶች ሰብረው ገብተው ለዘመናት ክርክር የተደረገባቸውና ውሳኔ የተሰጠባቸው እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ዕቅዳችን መፍትሄ የሚጠብቁ ፋይሎችን አቃጥለዋል።
የከተማ ከንቲባ /ቤቶችን፣ የማዘጋጃ ተቋማትን፣ ፖሊስ ጣቢያዎችን፣ ጤና ተቋማትን አቃጥለዋል። የከተማውን አመራሮችና ነዋሪዎች ቤትና ንብረት ዘርፈዋል፤ አቃጥለዋል። በከተሞቹ ውስጥ ኢንቨስት ያደረጉ ባለሀብቶችን ንብረት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ዘርፈዋል። አውድመዋል። የብሔርና የሃይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ ያለሙ ግድያዎችን በሰላማዊ ዜጎች ላይ ፈጽመዋል።
10
እነኚህ ቡድኖች በጸረ-ሰላምና በጸረ-ልማት ተግባራቸው የህዝብን የመልካም አስተዳደር እጦት ሊፈቱ የሚችሉ አይደሉም። የህዝብ ሀብት የፈሰሰባቸው መሠረተ ልማቶችንና መገልገያ ተቋማትን በማውደም ልማት አይመጣም ።የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብት ወደ ከተሞቹ ዳግም አንዳይደርሱ በማድረግ ህዝቡ አይጠቀምም የመልካም አስተዳደር ችግር በዚህ ዓይነት የተበተነና ከየአቅታጫው እየተጠራራ በተሰባሰበ ኃይልና ታጣቂ ቡድን ሊፈታ አይችልም።
ከሁከት ፈጣሪው ቡድን ጀርባ ሲቀሰቅሱና ሲያሰማሩ የነበሩ የትምክህት፣ የጥበትና የጽንፈኛ ኃይሎችም ቢሆኑ የተለያዩ የህዝብ ጉዳዮችን እያራገቡ ኑሯቸውን የሚገፉ፣ በየአጋጣሚው ሰላማዊ የሆነውን ህይወት በመበጥበት የሚኖሩ በመሆናቸው ህዝብ ያነሳውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈቱ አይደሉም። እንዳሰቡት በሁከት ህብረተሰቡ አፍ ከልብ የሆነበትን ህገመንግስታዊና ፌደራላዊ ስርዓቱን መቀየር ቢችሉ እንኳ ለህዝብ መልስ መስጠት ቀርቶ ተስማምተው መዋል እንኳ የሚችሉ አይደሉም።
ከአማራ ክልል የታየውም የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበርን ለማካለል የተጀመረ ስራ የለም፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር የምትካለለውን ድንበር በውል ለክታ ማወቋ በየትኛው መስፈርት ተገቢ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜ በነበሩ የሃገራችን መንግስታት በተለያዬ ደረጃ ሲነሳ የነበረ ሃሳብ ነው። የሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበር መካለልም በድንበር አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ጠቃሚ መሆኑም የሚካድ አይደለም።
የኢፌዲሪ መንግስት ሁሉም የኢትዮጵያ ድንበሮችን የማካለል ስራ ጠቃሚ መሆኑን ይረዳል። ድንበርን በተመለከተ ያለው መርህም የህዝብን ጥቅምና ሉአላዊነት ከማስጠበቅ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በተደጋጋሚ ተገልጿል። የኢፌድሪ መንግስት የድንበር ማካለል ስራ ሲኖር በድንበሮቹ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎቻችንን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንዲሆን ጽኑ አቋም አለው። ሆኖም የኢትዮ-ሱዳንን ድንበር ለማካለል አሁን ምንም የተደረገ ስምምነት የለም።
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ሊካለል ነው። ከኢትዮጵያ ሰፊ መሬት ለሱዳን ሊሰጥ ነው፣የሚሉ ምንጭ የማይጠቅሱ ዜናዎች በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ይመታየታቸውም አስተዋጽዎው ቀላል አልነበረም። ከጎንደር ሁከት ጋር ተያይዞም ሰፊ የመቀስቀሻ ሀሳብ ሆኖ ታይቷል፡፡ የዜናው ምንጮች የተለየ ዓላማ ከሌላቸው በቀር ዕውነቱ ግን በሁለቱ ሃገራት መካከል በጉዳዩ ላይ ምንም ውይይት እየተደረገ አለመሆኑ ነው።
የሂሳቡ ስሌት ይህ ከሆነ ደግሞ አክስረውናልና ሁከት በመፍጠር የዜጎች ህይወትና ንብረት እንዲጠፋ ምክንያት የሆኑ አካላት ተጋልጠው በህዝብና በህግ ፊት ሊዳኙ ይገባል።
ፌዴራላዊ ስርዓቱ ራስን የማስተዳደር እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ መብትን የመጠየቅ ዕድል አጎናፅፏል። ዜጎች ራሳቸውን ለማስተዳደር በየአራት ዓመቱ ተወካዮቻቸውን የሚሰይሙበት፣ ጥያቄያቸውን የሚያቀርቡበት ስርዓት ፈጥረዋል። የኢትዮጵያ ህዝቦች ብዝሐነታቸውን የሚያስተናግድ ስርዓት ገንብተው አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተጉ ነው።
ይህን በህገመንግስት ማዕቀፍ ስር እየዳበረ ያለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሁከት ለመናድ ያሰቡ ሃይሎች ህዝብና ሀገርን በድለዋል። ሀገርና ህዝብ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት አንድም ሰው በረሀብ እንዳይሞት በሚደክሙበት ወቅት እነኚህ ሃይሎች ሰላማዊ ዜጎች ህይወትና ንብረታቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆነዋል።
ሀገርና ህዝብ የገጽታ ግንባታ ስራ ላይ በመድከም የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ጥረት እያደረጉ እያለ የጥበትና ትምክህት ኃይሎች ግን ባለሀብቱን የሚጎዳና የሚያሸሽ፣ ገጽታን ለማበላሸት ምክንያት የሆነ ተግባር ፈጽመዋል። ፀረ ልማትና ፀረ ሰላም የሆኑት ሃይሎች በፈጠሩት ሁከት የተማሪዎች የትምህርት ጊዜ፣ የዜጎች ሰላማዊ ኑሮ ተጓጉሏል። ስለሆነም ከህዝብ ጋር በመሆን አጥፊዎች ሊጋለጡ በህዝብና በህግ ፊትም ሊዳኙ ይገባል።








                                            

No comments:

Post a Comment