ህዳሴ፡-
በቅድሚያ ለቃለምልልሱ ስለተባበሩን በአንባቢያን ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡ በከተማችን የሚ ስተዋለው የመልካም አስተዳደር ችግር
ምንጩ ምንድነው ይላሉ?
አቶ
ይስሀቅ፡- እኔም አመሰግናለው፡፡ ከትርጉሙ ስንነሳ መልካም አስተዳደር ዘርፈ ብዙ ትርጉም ነው ያለው፡፡ መልካም አስተዳደር ሲባል
የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው፣ ግልፅነት፣ የተጠቃሚነት ስርአት ማስፈን ነው፣ የህዝብ ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፣
ዋና ዋና በሆኑት የልማት እና የሰላም ጉዳዮች መግባባት መፍጠር ነው፡፡ እንዲህ ሰፋ ያለ ትርጓሜ ያለው ነው”” በተጨማሪ መልካም
አስተዳደር ሲባል መልካም ስራን ከመስራት ይመነጫል”” ህዝቡ የሚጠይቃቸው ጥያቄዎችን አግባብ ባለው መልኩ ህግና ስርአትን በመጠበቅ
ፈጣን የሆነ ምላሽ መስጠት ነው”” በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጉዳዮችም ህዝቡን በቅንነት ማገልገል ነው፡፡ ህዝብን
ማገልገል ክቡር እንደሆነ አስቦ መስራት ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ነጥቦች በምናይበት ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግር ምንጮችን ስንመለከት
ብዙ ናቸው”” ዋና መሰረቱ በየደረጃው ያለ አመራር የተመደበው ህዝብን ለማገልገልና የህዝብ ችግርን ለመፍታት ነው፡፡ የህዝብ ወገንተኛ
መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ችግሮች እየተፈጠሩ ያሉት የህዝብ ወገንተኛ ከመሆን ጋር የሚመነጩ ናቸው”” ህዝቡ መበደል፣ መሰቃየት የለበትም
የሚል የህዝብ ወገንተኝነት ማጣት ነው፡፡ በየደረጃው ያለ አመራር የህዝብ አገልጋይነት ስሜቱ በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑ ነው፡፡
በየደረጃው ያለው የመንግስት ሰራተኛ የተቀጠረው ህዝብን ለማገልገል መሆኑን በተመለከተ የተሟላ እምነት ይዞ አለመስራት ነው፡፡ ሁለተኛው
እላፊ ተጠቃሚነት ነው፡፡ ይህ ማለት የመንግስት እምነት በከተማው ልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ መመስረት ነው፣ ይህ ማለት ህብረተሰቡ
በየደረጃው የልማቱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ፍትሀዊ የሆነ የልማት ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ መፍጠር ነው፣ ስለዚህ ልማታዊ ፖለቲካል
ኢኮኖሚ እንደስርአት መመስረት አለበት”” ይህ ማለት አንዱ ተጠቃሚ
ሌላው የበይ ተመልካች የሚሆንበት ሳይሆን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃልል ስርአት መፍጠር ማለት ነው፡፡ አሁን በከተማው
የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰቡ በአመለካከትም በተግባርም የበላይ ሆኖ መልካም አስተዳደርን ማስፈን ትልቅ ፈተና እየሆነ ነው ያለው፡፡
ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም ባይሆንም ህብረተሰቡን የሚያጉላሉት የሚፈልጉት ነገር ስላለ ነው፡፡ በተቀመጠው አሰራርና ህግ መሰረት ከማገልገል
ውጪ አገልግሎትን በገንዘብ በጉቦ በመጠየቅ ለመጨረስ የመፈለግ አመለካከት በሲቪል ሰርቪሱም በአመራሩም ስላለ ታግለን ስላላስተካከልን
ነው፡፡ ስለዚህ ምንጮቹን በእነዚህ ሁለት መንገዶች መውሰድ እንችላለን፡፡ አንደኛው እላፊ መፈለግ፣ ሁለተኛው እላፊ ባይፈልግም በተቀመጠው
አሰራር መሰረት አመራሩና ፈፃሚው ህብረተሰቡን የማገልገል ክፍተት ነው፡፡
ህ
ዳ ሴ ፡- የ ተ ጠ ያ ቂ ነ ት ስ ር አ ቱ ጠ ን ካ ራ አ ለ መ ሆ ን ለ መ ል ካ ም አስተዳደር ችግር ዋነኛው ምክንያት ነው
ሊባል ይችላል? አ ቶ ይ ስ ሀ ቅ ፡ የተጠያቂነት ስርአቱ ተዘርግቷል፡፡ በዚህ ረገድ ምንም አልተሰራም ተብሎ ሊወሰድ አይቻልም፡፡ ባለፉት አመታት
በዚህ ተግባር ውስጥ የነበሩ አመራሮች፣ ሰራተኞች እንዲጠየቁ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ በ2007 ዓ.ም ከ200 በላይ አመራሮችና ከ4
ሺህ በላይ ሰራተኞች ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ተጠያቂነት ሲባል እንግዲህ የተለያየ ደረጃ አለው፡፡ ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው፣
ደሞዝ የሚቀጣ፣ ከስራ የሚሰናበት አለ ይህ ሁሉ ተጠያቂነት ነው”” በግምገማ የቃል ማስጠንቂያ የሚሰጠው አለ፣ ይህና ሌሎች መሰል
እርምጃዎች ተጀምረዋል፡፡ በዘንድሮው አመት ደግሞ የባለፈውን አመት ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ በተለየ መልኩ ነው የተጠያቂነት ስርአቱ
ላይ እየሄድን ያለነው፡፡ ዋና ዋና ሴክተር የሚባሉትን ህብረተሰቡ በብዛት የሚገለገልባቸውንና ለኪራይ ሰብሳቢነት ተጋላጭ የሆኑትን
ሴክተሮች የማጥራት ስራ እየሰራን ነው፡፡ በቀጣይ የሚጣሩ እንዳሉ ሆነው ለምሳሌ መሬትን ብንወስድ 22 ያህል አመራሮች /ከወረዳ
እስከ ክፍለ ከተማ/ ከመሬት ዘርፍ እንዲነሱ ተደርጓል”” 84 የሚሆኑ አመራሮች ላይ የቦታ ሽግሽግ ተካሄዷል፡፡ ይህ ተግባር አሁንም
ይቀጥላል፡፡ በሌሎች ሴክተሮችም በዚህ ደረጃ ማድረግ ይቻላል፡፡ ስለዚህ የተጠያቂነት ስርአቱ ተጀምሯል ማለት ነው፡፡ ሆኖም ያለው
ችግርና እየተወሰደ ያለው እርምጃ ምን ያህል ይጣጣማል የሚለው ነው ዋናው፡፡ ስለዚህ ከጅምር ያለፈ አይደለም፡፡ ጠንክረን መስራት
አለብን የሚለው መወሰድ አለበት”” ተጠያቂነት ሲባል ሁለት ነገሮችን የሚያካትት መሆን አለበት”” ተጠያቂነት ሲባል ያጠፋ ሰው ብቻ
እንቅጣ ማለት አይደለም”” ሁለት ስራ ነው፡፡ ከላይ እስከታች ያለውን ገምግመን ጥሩ የሚሰራውን ማበረታታት፣ ወደ ሃላፊነት እንዲመጣ
ማድረግ ነው፡፡ ጥፋተኛ የሆነውን ደግሞ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆን መስራት አለብን፡፡ ስለዚህ በተጠናከረ መልኩ እየሄድንበት
እንደሆነ ያሳያል፡፡ በእኔ እምነት መልክ ለማስያዘ ጥረት እያደረግን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው፣ ለምሳሌ ደንብ ማስከበርን በተመለከተ
ከላይ እስከታች ድረስ ያለውን አመራር አጥርተናል”” እዚህ ላይ በወረዳ 17 አመራሮች አይቀጥሉም፡፡ 10ሩ በኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር
ውስጥ የገቡ ሲሆኑ 7 ያህሉ በአቅም ማነስ ነው፡፡ 187 የሚሆኑ የደንብ ማስከበር ፈፃሚዎች ውስጥ 99 ያህሉ በኪራይ ሰብሳቢነት
ተግባር ውስጥ ተዘፍቀው በመገኘታቸው በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ ይህ ተግባር በዚህ ብቻ አያበቃም በሌሎች ሴክተር መስሪያ
ቤቶችም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ህዳሴ፡- 10ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ውሳኔን ተከትሎ በአዲስ አበባ
ከተማ የተሰሩ ስራዎች ምን ይመስላሉ? አቶ ይስሀቅ፡ ከጉባኤው በኋላ መጀመሪያ ያደረግነው የንቅናቄ ሰነድ የማዘጋጀት ስራ ነው የሰራነው፡፡
ምንም እንኳ ባለፉት አመታት መልካም አስተዳደር ላይ በሰራናቸው ስራዎች ለውጦች ቢኖሩም ነገር ግን ህዝብን የማገልገል፣ የህብረተሰብ
ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በምንፈልገው ደረጃ አለመሆኑና የዴሞክራሲያዊ ሂደቱን አጠቃላይ ሂደት ማጠናከር ላይ ህዝቡ ወሳኝ የሚሆንበት
ሁኔታ መፈጠር አለበት ነው የጉባኤው መንፈስ፡፡ እሱን መነሻ በማድረግ የንቅናቄ እቅዱ እንዲወጣ አድርገናል፡፡ አንደኛ ባለፉት አመታት
መልካም አስተዳደርን በተመለከተ የተካሄዱ ጥናቶች ነበሩ፡፡ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስተርና የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ከዋልታ ኢንፎርሜሽን
ማዕከልና በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በመልካም አስተዳደር ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ የተጠኑ ጥናቶች ነበሩ፡፡ ችግሩን ለመፍታት ምን
አይነት ምቹ ሁኔታ አለ የሚለውን ከግምት በማስገባት ነው የንቅናቄው እቅድ የተዘጋጀው”” ይህ እቅድ ከተዘጋጀ በኋላ በሚመለከታቸው
አካላት እንዲፅድቅ ነው የተደረገው፡፡ እቅዱ ከፀደቀ በኋላ ቀጥሎ ያደረግነው ለአመራር አካላት ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ከ3 ሺህ
በላይ የሚሆን አመራር በዚህ እቅድ ላይ እንዲወያይ ተደርጓል፡፡ በመቀጠል ከቀጠና እስከ ከተማ ድረስ ከ300 ሺህ በላይ ህብረተሰብ
እንዲወያይ ተደርጓል፡፡ በውይይቱ ጊዜ ህብረተሰቡ በጣም ጠቃሚ የሆነ ለእቅዱ ግብአት የሚሆን ሀሳብ ሰጥቷል፣ ስለዚህ 10ኛው ጉባኤ
የመልካም አስተዳድር ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነው ብሎ ባስቀመጠው መሰረት ከላይ እስከታች ህብረተሰቡ በጉዳዩ ላይ እንዲሳተፍ የተደረገበት
ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይህ አንዱ ከጉባኤው በኋላ የሰራነው ህብረተሰቡን በነቂስ የማሳተፍ ስራ ነው፡፡ ሁለተኛው ችግሩን ለይተን ነበር
ሆኖም ህብረተሰቡን ስናወያይ በእቅድ ያልዳሰስናቸው በጣም በርካታ ችግሮች እንዲታዩ ነው የሆነው”” ስለዚህ ጉባኤው በዋናነት ያስቀመጠውን
ህብረተሰቡን የማሳተፍ አቅጣጫ ይዘን በመሄዳችን በርካታ ግብአቶችን አግኝተናል፡፡ ህብረተሰቡ የሰጠንን አስተያየት ለቅመን በእቅዱ
እንዲካተት አድርገናል፡፡ በዚህ መሰረት በፌዴራል፣ በከተማ፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ የሚፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተለይተዋል፡፡
ለምሳሌ በዚህ አመት በወረዳ ብቻ የሚፈቱ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች 1820 ናቸው፡፡ በክፍለ ከተማ 647፣ በከተማ 330 እንዲሁም
በፌዴራል ደረጃ 84 ያህል ናቸው፡፡ እነዚህን ለየብቻ ለቅመን ለየባለቤቱ ቆጥረን ሰነድ አዘጋጅተን አስረክብናል”” ስለዚህ በቀጣይ
ተጠያቂነት አለ ማለት ነው፡፡ የትኛው እርከን የቱን ይፈታል የሚለውን መነሻ አድርገን ወደ ስራ ገብተናል፡፡ ሌላው አቅጣጫ ምንድነው
በመቀለ ጉባኤ መሰረት ይህንን የመልካም አስተዳደር ጉዳይ እያወሳሰቡ ያሉ ችግሮች ሁለት ናቸው”” አንደኛው የውስጥ ሃይል ኪራይ
ሰብሳቢና ሁለተኛው በውጭ ያለው ደላላው ኪራይ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ ስለዚህ የውስጥ ኪራይ ሰብሳቢውን እያጠራን እየለየን ነው፡፡ ዋናው
ጉዳዩን ውስብስብ ያደረጉት ውስጥ ያለውና ውጭ ያለው ኪራይ ሰብሰቢ ሀይል በአንድነት ሆነው ነው”” ስለዚህ በሁሉም ሴክተር በመሬት፣
በንግድ እና በሌሎች ሴክተሮች ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የንቅናቄውን እቅድ ማዘጋጀት የክትትልና ድጋፍ ማንዋል ቼክ ሊስት፤ ስራን
ቆጥሮ ለየባለቤቱ
የመስጠትና ባለድርሻዎቹ በእኔነትና በባለቤትነት ስሜት ስራውን
ወስደው እንዲሰሩ ማድረግ ነው፡፡
ህ ዳ ሴ ፡- ች ግ ሮ ች ን ከ መ ለ የ ት ና ለ ሚ መ ለ
ከ ተ ው አ ካ ል ቆ ጥ ሮ ከመስጠት ጎን ለጎን እስከአሁን ያለው እርምጃ ምን ይመስላል? አቶ ይስሀቅ፡ አሁን ወደስራ ገብተናል፡፡
በቅርብ ጊዜም ገምግመን ነበር፡፡ በመሬት ላይ የማጥራት ስራው እንዳለ ሆኖ ከዚህ ጎን ለጎን ሰነድ አልባ ላይ በዚህ አመት 44
ሺህ ካርታ እንሰጣለን ብለን አቅደን እስከአሁን ወደ 14ሺህ 500 የሚሆን ካርታ አትመናል”” ከዚህ ውስጥ 15 በመቶ ያህሉ ብቻ
ነው ካርታውን ክፍለ ከተማ ሄዶ የወሰደው፡፡ ሌሎች በመሬት ላይ የሚሰሩ ስራዎችንም ሰርተናል”” ካርታው ታትሞ ህብረተሰቡ በጊዜ ካርታውን የመውሰድ ክፍተት አለበት፡፡ በግንባታ
ፈቃድ ላይ የነበሩ ችግሮችም ተቆጥረው እየተሰሩ ነው ያሉት፡፡ በአጠቃላይ ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚነሱ አግባብነት ያላቸው
ጥያቄዎችን ለመመለስ በሙሉ አቅም እየሰራን ነው፡፡ ሌላው ንግድ ላይ የኮንትሮባንድ ንግድን በፌዴራል በከተማም ኮሚቴ በማዋቀር የቁጥጥር
ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ የሸማቶች የህብረት ስራ ማህበራትን ተደራሽነት የበለጠ ለማጠናከር ተጨማሪ 47 መሸጫ መደብሮችን ጨምረናል፡፡
የግብይት ስርአቱ ላይ ያለውን ስርቆት ለማስቀረት እርምጃዎች ጀምረናል፣ አለአግባብ ዋጋ የጨመሩ፤ ሆን ብለው ሰው ሰራሽ የምርት
እጥረት ለመፍጠር የሞከሩ አካላትም ተጠያቂ እንደሆኑ ተደርጓል፡፡
ህዳሴ፡- በዚህ ዙሪያ የህዝብ ክንፍ ምን ያህል እየተሳተፈ ነው?
አ ቶ ይ ስ ሀ ቅ ፡ ከላይ የጠቀስኩት እንደተጠበቀ ሆኖ ህዝቡን ለማሳተፍ በአጠቃላይ ከከተማ እስከ ወረዳ የተሰራ ስራ አለ””
52 የሚሆኑ ተቋማት አሉ በከተማ እነዚህ ተቋማት የህዝብ ክንፎቻቸውን ጠርተው አወያይተዋል፣ 63 ሺህ የሚሆን ህብረተሰብም ተሳታፊ
ሆኗል፡፡ ህዝቡ አሉ የሚላቸውን ችግሮች ማንሳት ብቻ ሳይሆን የመፍትሄውም አካል እንዲሆን ተደርጓል”” በተመሳሳይ በክፍለ ከተማ
1260 ተቋማት አሉ፡፡ እነዚህም የህዝብ ክንፎቻቸውን ለይተው ወደ ተግባር ገብተዋል፡፡ በወረዳ ደረጃም 2 ሺህ 476 የሚሆኑ ሴክተሮች
አሉ እነዚህም በተጨባጭ ህብረተሰቡን አሳታፊ በማድረግ እየሰሩ ነው፡፡ ህብረተሰቡ በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ ህገ ወጦችን
ችግር ያለባቸውን አካላት ስም ዝርዝር እየጠራ ጭምር በማጋለጥ ላይ ነው፡፡ እኛም ይህንን የህዝብ ጥቆማ ይዘን 40 የሚሆኑ ወረዳዎችን
ለይተናል፡፡ ወረዳዎችንም ባወያየንበት ወቅት ህዝቡ የአመራሩን ስም ጭምር በማንሳት እየጠቆመ ነበር፡፡ በቀጣይ እስከ አሁን ከፌዴራል
እስከ ወረዳ ድረስ የሰራነውን ስራ ለህዝቡ ማቅረብ ነው፡፡ ቀጣይ የበለጠ ትግል የሚጠይቀውንና የሚቀረንን ማሳየት ነው፡፡ ከዚህ
ቀደምም በእቅዳችን በአጭር ጊዜ፣ በመካከለኛ ጊዜ፣ በረጅም ጊዜ የሚፈቱ
ብለን በለየነው መሰረት ማለት ነው፡ ፡ ሌላው በህዝብ ተሳትፎ ያጠራነውን ጨምሮ 1536 አመራር በትምህርትና በኪራይ ሰብሳቢነት
ተነስቷል፡፡ 262 ያህሉ በኪራይ ሰብሳቢነት ችግር መሆኑን ለህዝቡ አቅርበናል፡፡ ህዝቡም ትክክል ነው፡፡ ጥፋተኛ የሆኑትን መጠየቃችሁ
ትክክል ነው ብሎናል፡፡ በትምህርት የተነሱትንም አዎንታዊ በሆነ መልኩ ነው የተቀበለው”” ስለዚህ በቀጣይ የሚቀረን ምንድነው ለህዝቡ
የሰራነውን ማቅረብ”” በሚቀረን ስራ ላይም መመካከርና ቀጣይ ስራዎች ላይ መግባባት ነው፡፡
ህዳሴ፡- የአገልግሎት አሰጣጥ እንግልትን ከማስቀረትና በመንግስት
የስራ ሰአት የሚደረጉ ስብሰባዎችን ወጥ የሆነ መልስ ከማስያዝ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ምን ይመስላሉ? አ ቶ ይ ስ ሀ ቅ ፡
ዋናው መልካም አስተዳደር ሲባል ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ላይ ያለው ችግር ነው፡፡ ስለዚህ ይህን እንግልት ለማስቀረት ከዚህ ቀደም
የባለጉዳይ ቀን ተወስኗል፡፡ ሰኞ፣ እሮብና አርብ በወረዳ እሮብና አርብ እንዲሁ በክፍለ ከተማ ባለጉዳዮች ይስተናገዳሉ፡፡
በመመሪያችን መሰረት ስብሰባ ከ10 ሰአት በኋላ እንዲሆን ተወስኗል”” ሰርኩላርም ወርዷል፡፡ መሻሻሎች አሉ”” አሁንም ቢሆን ግን በባለ ጉዳይ ቀን
ስብሰባዎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ በቀጣይ ማስተካካል አለብን፡፡ አሁንም ስብሰባ የሚጠራ አለ፡፡ ቢሮው የማይገኝ አመራር አለ፡፡
ይህን በቀጣይ እናጠራለን”” ለምሳሌ በከተማ ደረጃ የአገልግሎት እስታንዳርድ አለ በቀን እና በሰአት ጭምር ተሸንሽኖ በዚህ መንገድ
ይሰራ ነው የሚለው ስታንዳርዱ ጊዜን መጠንን ወጪና ጥራትን አቀናጅቶ በመስራት በኩል መሻሻል ቢኖርም በሚፈለገው ደረጃ አይደለም፡፡
ወደ 1400 የሚሆኑ የአገልግሎት ስታንዳርዶች አሉ፡፡ ዋናው ምክንያት እኔ የተቀጠርኩት ህዝብን ለማገልገል ነው የሚል አስተሳሰብ
በሚፈለገው ደረጃ አለመያዝ ነው፡፡ አንድ ሰራተኛ እቅዱን በውጤት ተኮር የምዘና ስርአት ማዘጋጀት አለበት፡፡ በከተማው 54 ሺህ
ያህል ሰራተኛ እቅዱን በውጤት ተኮር የምዘና ስርአት በማቀድ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ ይህም ከአጠቃላይ 85 በመቶ ያህል ነው፡፡
ይህ ነው አሁን ያለው፡፡ በአመት ሁለት ጊዜም ሰራተኛውን እንመዝናለን፡፡ በቅርቡም ወደ ምዘና የሚገቡ ተቋማት አሉ፡፡ እስከ የካቲት
አጋማሽ ይጠናቀቃል፡፡ በዚህም እያንዳንዱ ተቋም በምን አይነት አቋም ላይ እንዳለ ይታወቃል ማለት ነው፡፡ የትኛው ነው በተሻለ ህብረተሰቡን
እያገለገለ ያለው የትኛው ነው ወደኋላ የቀረው የሚለውንም እንለያለን””
ህዳሴ፡- የወረዳዎችን የክፍለ ከተሞችን አቅም በሰው ሀይልና
በግብአት ከማሳደግ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ምን ይመስላሉ? አ ቶ ይ ስ ሀ ቅ ፡ የማስፈፀም አቅም የሶስት ጉዳዮች ጥምረት
ውጤት ነው፡፡ እነዚህም የሰው ሀይል፤ የግብአትና የአደረጃጀት ነው እስከ አሁን ድረስ በከተማችን 85 ሺህ ያህል የመንግስት ሰራተኛ
አለ”” ከዚህ ውስጥ 28 ሺህ ያህሉ ዲግሪና ከዛ በላይ ነው፡፡
54 ሺህ ያህሉ ዲፕሎማና ከዛ በታች ነው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ የወረዳና የክፍለ ከተማን አጠቃላይ የሰው ሀይል ለማጠናከር እየተደረገ
ያለው ጥረት በ3 መልኩ ነው፡፡ አንደኛ መማር ያለበትን ሰራተኛ በነፃ እያስተማርን ነው፣ በከተማ ሴክተር ተቋማት ብቻ ከ240 በላይ
ሰራተኞችን በኮተቤ ዩኒቨርስቲ እያስተማርን ነው”” በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲም እንዲሁ ከ250 በላይ ሰራተኞችን የትምህርት ደረጃቸውን
እንዲያሻሽሉ በነፃ እያስተማርን ነው፡፡ ሁለተኛ ወረዳዎችም ሆነ ክፍለ ከተሞች ላይ ያለውን የሰራተኛ ፍልሰት ለማስተካከል የቢሮዎችን
አደረጃጀትና አሰራር በመፈተሽ እየሰራን ነው፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት ያላቸውን የስራ መደቦች በመለየት አዲስ የዩኒቨርስቲ
ተመራቂ ተማሪዎችን በማሰልጠን ወደ ስራ ለማሰማራት በሂደት ላይ ነን”” በዚህ መልኩ የሰው ሀይሉን ለማጠናከር እየሰራን ነው ያለነው፡፡
የወረዳዎችን የማስፈፀም አቅም ግንባታን በሰው ሀይል በአደረጃጀት በአሰራር መደገፍ ላይም ትኩረት ሰጥተናል፡፡ ሌላው ከተማ አቀፍ
የመዋቅርና የአደረጃጀት ስራ እየሰራን ነው”” አሁን ከተማው የደረሰበትን እድገት ሊመራ የሚችል አሰራር ለመፍጠር ኘሮጀክት ጽ/ቤት
አዋቅረን እየሰራን ነው፡፡ በዚህ አመት ዝግጅቱ ተጠናቆ በመጪው አመት ወደ ተግባር ይገባል፡፡ በዚህም ቢያንስ ለ10 አመት በጥራት
ሊያገለግል የሚችል መዋቅር ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ ሌላው ይህ መዋቅር የአገልግሎት ስራዎቹን በማዘጋጃ ቤታዊ አሰራር እንዲመራ ማድረግ
ይህም የፖለቲካ አመራሩ የራሱን ስራ ብቻ የሚሰራበትን መንገድ ለመዘርጋት ነው፡፡ ወረዳዎች ላይ ያለውን የመሳሪያ በጀት እጥረት
ለመቅረፉ በአስተዳደር በኩል የሚሰራው ስራ እንዳለ ሆኖ በፐብሊክ ሰርቪስና በሰው ሀይል ቢሮ በኩል ለወረዳ ብቻ ለግብአት ማሟያ
ወደ 23 ሚሊዮን ብር መድበናል፡፡
ህ ዳ ሴ ፡- መ ል ካ ም አ ስ ተ ዳ ደ ር ን በ ሚ ፈ ለ
ገ ው ደ ረ ጃ ለ ማ ስ ፈ ን በቀጣይስ የህዝቡ ሚና ምን መሆን አለበት? አ ቶ ይ ስ ሀ ቅ ፡ የህብረተሰቡ ሚና የማይተካ ነው፡፡
በመልካም አስተዳደር ዋና ተጎጂውም ተጠቃሚውም ህብረተሰቡ ነው፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ ትልቅ ሀላፊነት ነው ያለበት፡፡ የመንግስት
እይታ ውስን ነው፡፡ የህዝብ እይታ ግን ሰፊ ነው፡፡ ከህዝብ የሚያመልጥ ምንም ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ከህብረተሰቡ የሚጠበቀው ሚና
ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያውና ዋናው በዝግጅት ምዕራፍ እንዳደረገው ሁሉ በተግባር ምዕራፍም የጀመርናቸውን የመልካም አስተዳደር ስራዎች
ውጤታማ እንዲሆኑ እራሱ ባለቤት መሆን አለበት፡፡ ችግሮች በሚታዩ ጊዜ ችግሮች በዚህ በዚህ መንገድ አሉ ሊቀጥሉ አይገባም ማለት
አለበት፡፡ የባለቤትነት ስሜት መያዝ አለበት፡፡ ትግል የምናደርገው እሱን ይዘን ነው፡፡ ስለዚህ ዋና ተዋናዩ ዋና ዳኛው ተጠቃሚ
ህዝቡ ነው፡፡ ዋና ፈራጅም እሱ ነው ስለዚህ ትልቅ ሚና አለው፡፡ በተጨባጭ ለአብነት ለማየት ባለፉት አምስት አመታት በከተማ የተሰሩ
የአካባቢ ልማት ስራዎችን ማንሳት እንችላለን፡፡ እስከ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ አድርጎ በርካታ የአካባቢ ልማት ስራዎችን ሰርቷል፡፡
ይህ የማይተካ ሚና ነው፡፡ ህዝቡ ከኪራይ ሰብሳቢነት ትግል አንፃርም የጀመረውን የማጋለጥ ስራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ኪራይ
ሰብሳቢነት፣ እላፊ ተጠቃሚነት የግለሰብ ጉዳይ ሳይሆን የስርአት ጉዳይ ነው፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት ካለ መልካም አስተዳደር ልማት ሰላም
ማምጣት አይቻልም፡፡ ይህ ማለት በከተማችን የጀመርነው ልማትና የህዳሴ ጉዞ አስተማማኝ እንዲሆን ከተፈለገ ህብረተሰቡ በፀረ ኪራይ
ሰብሳቢነት ትግሉ ላይ ትልቅ ሚና ሊወጣ ይገባል፡፡ ለህግ የበላይነት ሊቆም ይገባል፡፡
ህዳሴ፡- ለነበረን ቆይታ በአንባቢያን ስም በድጋሚ አመሰግናለው
”” አቶ ይስሀቅ፡ እኔም አመሰግናለው፡፡
እንደአጠቃላይ የቀረበው ነገር መረጃ ለህዝብ ከ።መስጠት አንፃር ጥሩ ነው። ከዛ ውጭ ሊያወያዩን የሚገቡ በርካት ነጥቦች ቢኖሩም እንኩወዋን ሁለት ጉዳዮችን ማንሳት እፈልጋለሁ። የመጀመሪያው የመልካም አስተዳደር ችግር ጥምርታ በፌደራልና ወረዳ መካከል ያለውን በተገልጋዪ ህዝብ ላይ የሚፈጥረውን ጫና ይሆናል። በዘገባው እንደተባለው 84 ችግሮች በፌደራል ደራጃና ከ1848 ችግሮች በወረዳ ላይ ይስተወላሉ ቢባል እንኩዋን አንድ ችግር በፌደራል ደረጃ ስትፈጠር በአማካይ 18 ያህል ችግሮች በወረዳ ደረጃ ይከሰታሉ ከማለትም በተጨማሪ አንድን ባለጉዳይ እስከ 1848 ያህል ችግሮ በተለያዩ ጊዜያት ሊደርስበት ይችላል ማለት እንደሆነ ላስተዋለ ሰው ጉዳዩ እጅግ ዘግናኝ እንደሆነ ነው። ሁለተኛው ነጥቤ ደግሞ የአቅም ችግር ያለበት አቅሙን ከመገንባቱ በተጨመሰሪ ወደሚመጥነው ቦታ መሸጋሸጉ አስፈላጊ ቢሆንም እርምጃው ሙሰኛንና ኪራይ ሰብሳቢን ከማጥራትና ማንገዋለል ገሰር ለምን ተጣመረ? ምናልባትም እንዲቆይለት የሚፈልገውን ኪራይ ሰብሳቢ በአቅም ውስንነት ሽፋን ለመደበቅ እንዲያመቸው ተደርጎ ቢሆንስ?
ReplyDelete