***Save water and reduce pollution***
ትላልቅ
ሞሎች
የቤጂንግ
መገለጫ
ይመስላሉ፡፡
እዚህ
ሀገርዎ
ሆነው
እንደሚያስቡት
‹‹ ደግሞ
ለቻይና
እቃ ብለው›› ጥቂት መቶ ብሮች/ ዩአን ይሉታል የብር ኖታቸው/ ይዞው ወደ እነዚህ ሞሎች ብቅ ቢሉ በሚያይዋቸው እቃዎች ምራቅዎ ሊጨምር ይችላል፡፡ ጠጋ ብለው የተፃፈው ሲመለከቱ ግን አመድዎ ቡን ይላል፡፡ ለአንድ የሴት ሙሉ ልብስ/ ሶስት በአንድ የሚባለው/ 10
ሺህ ዩአን ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ በኛ በሶስት ምቱት፡፡ ወዳጄ እዚህ ጋ ‹‹ለዛውም ለቻይና እቃ›› የሚለው አይሰራም፡፡
ከሌለዎት
አራት
ዩአንዎን
/በኛ
14 ብር
ገደማ/
ከፍለው
በሳቦይ
ወደ ሲልክ የሚባለው ገበያ ማምራት ይኖርብዎታል፡፡
በአይን
እይታ
ባይለይቱም
በሞል
በሺ ብር የተጠየቁበት እቃ በጥቂት አስር ዮአን ወይም መቶዎች ብሮች ያገኙታል፡፡ አዎ በጂንግ ዛሬም ቢሆን ለአንዱ አልብሳ ሌላውን እርቃኑን የሚሳደር አንጀት የላትም፡፡ በያዙት ሆቴል ለአንድ ምግብ እስከ 300 ዩአን ወይም 900 ብር፣ ለአድ ቢራ 30 ዩአን ወይም 110 ብር ገደማ ሲጠየቁ አረ እሳት የሆነ ንሮ ቢሉ አይፈረድብዎትም፡፡
ግን አይዞት ዞር ዞር ካሉ ቢራን በሶስት ዮአን በርገርም ከ30 እስከ 15 ዮአን ያገኛሉ፡፡ አንድ ወዳጄ ፓስታን በ13 ዮአን መብላቱ ነግሮኛል፡፡
40 ብር
መሆኑ
ነው፡፡
የቤት
ኪራይ
ግን እሳት ነው፡፡ እናም አብዛኛው ነዋሪ ከመሃል ከተማዋ ርቆ ነው የሚኖረው፡፡ የሚበዛው በአምስተኛ ቀለበት ነው የሚኖረው ብለኛለች ስታር፡፡ ፀጉረ ልውጥ ብርቅ በሆነበት ቤጂንግን እንዲህ ስቃኛት ውዬ አልጋየ ላይ ጋደም አልኩኝ፡፡ በራስጌ ያሉ ወረቀቶች አንዱን አነሳሁኝ፡፡ በፍፁም ያልጠበኩት ማሳሰቢያ ተፅፎ አየሁኝ፡፡
እንዲህ
የሚል
በትህትና
የተሞላ
የትብብር
ደብዳቤም
አነበብኩ፡፡