ዮናስ
የአዲስ
አበባ ማስተር ፕላን ገና ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ተግባራዊ ሲሆን የሚነካ ሰው፣ ቅሬታውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ማስተር ፕላኑን ከኦሮሚያ ጋር የሚያያይዘው ጉዳይ ቢኖር ይሄ ማስተር ፕላን በሚተገበርበት ጊዜ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች ተነጥለው የሚቀሩ ከሆነ፣ ከአዲስ አበባ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም ሳያገኙ ይቀራሉ የሚል እንደሆነም ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሲሠራ፣ አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች የማስተር ፕላኑ አካል ሆነው ቢሠሩ ከአዲስ አበባ ሊያገኙ የሚችሉትን ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ይሄማለት አዲስ አበባ በአዲስ አበባ፣ የኦሮሚያ
ከተሞች በኦሮሚያ እየተዳደሩ
ማለት መሆኑም ግልጽና የማያሻማ
ነው፡፡
ይህ
በእንዲህ እንዳለ ግን አንደኛው ወገን ሕዝብ ለማነሳሳት ሲፈልግ፣ አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ነው ብሎ ይቀሰቅሳል፡፡ ይህ በጭራሽ ያልታሰበና ሊሆንም የማይችል ነው፡፡ አዲስ አበባ የራሷ ድንበር አላት፡፡ ከድንበሩ አንድ ኢንች ወደ ኦሮሚያ አትገባም፡፡ አሁን የታሰበው ማስተር ፕላኑ በጋራ ቢሠራና የጋራ ተጠቃሚነት ይኖራል በሚል ነው፡፡ ለምሳሌ የባቡር መሠረተ ልማት ሲዘረጋ አዲስ አበባ ወስዶ ጫፍ ላይ ቢያቆም፣ ኦሮሚያ ከተማ ውስጥ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ ባቡር የሚጠቀሙት ዕድል ዝግ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ማስተር ፕላን እስከ ኦሮሚያ ከተሞች ድረስ ቢሄድ የባቡር መስመሩ በዚያ ቢለይ፣ የአዲስ አበባ የውስጥ መስመር እስከ ኦሮሚያ ከተሞች ድረስ ቢዘልቅ፣ በኦሮሚያ ያለው ኅብረተሰብ ከአዲስ አበባ ጋር በንግድም ለመተሳሰር ይጠቅመዋል ማለት እንደሆነም ይታወቃል፡፡ ኤሌክትሪክና ውኃ ሲዘረጋም በተመሳሳይ መንገድ ማለት ነው፡፡
አዲስ አበባ እያደገች የኦሮሚያ ከተሞች እየቆረቆዙ ከሄዱ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ የምታገኘውን ጥቅም ታጣለች ማለት ነው፡፡ የአዲስ አበባ ዕድገት ለኦሮሚያ ከተሞች ጥቅም ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ አንድምታ የሌለውና አዲስ አበባ ዙሪያ ላይ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች ምንም ዓይነት ጥቅም የሚያጡበት ሳይሆን፣ ጥቅም የሚያገኙበትና ተያይዞ የማደግ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አንዱ የአንዱን የመውሰድ ጉዳይ እንዳይደለ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
ከአዲስ
አበባና ከኦሮሚያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች ያላቸው ወይም አለን የሚሉ ተማሪዎች በተወሰኑ የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ እንቅስቃሴዎች ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ሲጀመር እንቅስቃሴው በስፋት በተከሰተባቸው ሦስት ዞኖች ውስጥ የሁከትና የብጥብጥ የተወሰነ ባህሪ የነበረው ቢሆንም፣ በወሳኝ መልኩ ወደለየለት ሁከት ያመራ ነው ተብሎ አይወሰድም፡፡
ጥያቄው
የማስተር ፕላን ጥያቄ ነው ወይ የሚለውን በሁለት ነገር ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ የነበረውም ብዥታ በቂ ማብራሪያ ካለመሰጠቱ ጋርና በዚህ ጉዳይ ላይ በርካታ ተረት የተወራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ በጉዳዩ ላይ ብዥታ ያደረባቸው ለፌዴራል ሥርዓቱ በየዕለቱ መጠናከር የተሟላ ቁርጠኝነት ያላቸው ወገኖች በውሸት ፕሮፖጋንዳ ላይ ተመሥርተው ሥጋት ውስጥ መግባታቸው የሚገርም ነገር አልነበረም፡፡ ከመነሻው አንዳንዳቹ ይኼ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የሚባለው ነገር የአዲስ አበባ ከተማን ግዛት በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞች ላይ ለመጫን የተደረገ ነው ብለው ቢሰጉ፣ ለፌዴራል ሥርዓቱ ካላቸው ቀናዒነት የመነጨ ስለሆነ ብዙ የሚያስገርም ሊሆን አይችልም፡፡ በትክክል ሥጋት ኖሮት በዚያ ሥጋት ላይ ተመሥርቶ አቋሙን በአንድ ወይም በሌላ መልኩ መግለጽ የፈለገ የኅብረተሰብ ክፍል የነበረ መሆኑ ይታወቃልና፡፡
የተጀመረውን
የተቀናጀ ማስተር ፕላን በተመለከተ ማብራሪያ በመስጠት በኩል በክልልም፣ በፌዴራል መንግሥትም ባለሥልጣናት መዘግየት የነበረ መሆኑንም መዘንጋት አይገባም፡፡ ትክክለኛ የሕዝብ ጥያቄን እንደ አጋጣሚ መጠቀም የሚፈልጉ ወገኖች ነበሩ፡፡ እነዚህ ወገኖች ባለፈው ምርጫ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ሥልጣን ለማግኘት የሚያስችል ቁመና ሊፈጥሩ ሞክረው ያልተሳካላቸው እና ጠባብ ብሄርተኝነትን የሚያቀነቅኑ ናቸው፡፡ ድሮውንም ከማስተር ፕላኑ ጋር የተያያዘ ጥያቄ አልነበራቸውም፡፡ ችግሩን በማራገብ
በተለይም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ወጣቶችና ሕፃናት መሣሪያ እስከመንጠቅ የደረሰ ትንቅንቅ እንዲያደርጉ ከፍተኛ ዘመቻ አድርገዋል፡፡
በዚህም
ቁጥሩ የማይናቅ ዜጋ የሞት አደጋ ደርሶበታል፡፡ ይኼ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ጥያቄው ቀድሞ በተነሳበት ሁኔታ የአንድም ሰውም ቢሆን አካል መጉደል ሊያስከትል የማይገባው ነው፡፡ ጥያቄው በተሳሳተ መንገድ ስለተመራ ላላስፈላጊ ጉዳት ምክንያት ሆኗል፡፡
ጥያቄ
መያዝ አንድ ነገር ሆኖ ጥያቄውን የምናቀርብበት አግባብ ግን ሥርዓትን የሚያጠናክር እንጂ የሚንድ መሆን የለበትም የሚል ጠንካራ አቋም በአብዛኛው የኦሮሚያ ተወላጅ የተንፀባረቀ ነው፡፡ ችግሩም ያስከተለው አደጋ ሊቀንስ የቻለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ በተለይ ሁከቱንና ብጥብጡን በመምራት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ወገኖች የሚፈልጉት ወደለየለት ብጥብጥ፣ ዘረፋና ሥርዓት አልበኝነት ተገብቶ በዚያች አጋጣሚ በሚፈጠረው ግርግር ኅብረተሰቡ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ነው፡፡ እነዚህ ሥርዓቱ የወለዳቸው፣ ሥርዓቱ ሕዝባዊነቱን ለማስመስከር ብሎ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ የታዩ ድክመቶችና ጉድለቶች የሚፈቱት ሥርዓቱን ባከበረ፣ ከምንም ነገር በላይ አዎንታዊ ብለን ባስመዘገብናቸው ጉዳዮች ላይ የበለጠ መጠናከርን፣ ባሉብን ድክመቶች ደግሞ የተሻለ አፈጻጸም ሊያመጣ በሚችል መልኩ መሆን አለበት ፡፡ የተፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሙሉ ወደ ሁከት ያመራሉ ማለት አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ
ከ80 በላይ የተለያዩ ማንነቶች ያቀፈች ሃገር መሆኗን መቼም መካድ አይቻልም፡፡ እነዚህ ማንነቶች ባለፉት የዘውድና ወታደራዊ አገዛዝ ዘመናት ማንነታቸውን እንዲሸሽጉ ወይም ጨርሰው እንዲፍቁ የተገደዱበት ስርዓቶች እንደነበሩም እንዲሁ፡፡ በነገስታቱ ዘመን የኢትዮጵያዊነት መለኪያ የራስ ማንነትን በመተው የገዢዎችን ቋንቋ፣ ባህልና ሃይማኖት መልበስ፣ ዘውዳዊ ስርዓቱ የደገፈውን ሁሉ መከተልና መስሎ መታየት የነበረ መሆኑንም ዛሬ ተቃዋዎቹ ሊክዱ ቢሞክሩም ታሪክ የመዘገበው እውነትና ይልቁንም የክህደታቸው መነሻ ይህንኑ ስርዓት መመለስ መሆኑን በርካታ የፖለቲካ ተመራማሪዎች
ያረጋገጡትና በተግባርም አሁን ካለው ተጨባጭ እንቅስቃሴያቸው የተገነዘብነው ሃቅ ነው፡፡
በመሳፍንታዊ
ስርዓተ- መንግስት አንድ ሃገር የመፍጠርና የማቃናት ሂደት አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህል፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ማንነትና አንድ ሃገር በሚል ፍልስፍና ማንነትን በማፈን የተከናወነ ሆኖ ከኢኮኖሚ ጭቆና ጋር በማስተሳሰር የተፈፀመ መሆኑም እሙንና ልካደውም ቢሉ የማይቻል ነው፡፡ በነገስታቱ ዘመን ሌሎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችም የማይታሰቡ ስለነበር የሥርዓቱ ፍፁማዊነት ‹‹ንጉሥ አይከሰስ ሠማይ አይታረስ›› በሚል ብሂል ይገለፅ እንደነበረም የቅርብ ጊዜ ትውስታና የኢትዮጵያ ታሪክ አካል ሆኖ በነገስታቱ ዘመን የታሪክ ድርሳናት ላይ የመጀመሪያ ገፅ የሰፈረ እውነት ነው፡፡
ይህንን
ማንነታቸውን የነጠቀውን ሥርዓት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለማስከበርና ለማስመለስ የጀመሩትን ተጋድሎ ተከትሎ በአቋራጭ ስልጣን የነጠቀው የደርግ አስተዳደርም ለጭቁኑ ህዝብ የቆምኩ ነኝ ብሎ ወንበሩን ካደላደለ በኋላ ትግሉን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት አስከፊ ጭፍጨፋ መፈፀሙም የዚህ ትውልድ ታሪክ በመሆኑ እንዲረሳ የተለያዩ የስነልቦናና የታሪክ መፅሀፍት ትግሎች ቢደረጉም ሊሳካ አልቻለም፤ አይችልምም፡፡ ማንነትን የማስከበርና የማረጋገጥ የመብት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ማንሳት ይቅርና ማሰብ ራሱ በህይወት የሚያስቀጣ አምባገነናዊ ስርዓት የነበረ መሆኑን የሚክዱትና አሁን በአዲስ መልክ ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱት ሃይሎች አብዛኞቹ የዚያው አምባገነናዊ ስርዓት አካልና አጋፋሪ የነበሩ መሆናቸው በመሰረቱ አፅንኦት ከተሰጠው ክህደታቸውና አሁን የጀመሩት ግርግር መነሻ ግልፅ ይሆናል፡፡
ደርግ
በመሳፍንታዊ ዘመን የነበረውን የአንድ ሃይማኖት የበላይነት በመሰረቱ ሳይቀይር ነገር ግን ለውጥ ያመጣ በማስመሰል ሁሉም ሃይማኖቶች እምነታቸውን በነፃ እንዳያራምዱ አፍኗል፡፡ የሃይማኖት ተቋማትን ዘግቷል፡፡ በርካታ አማኞች አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ ይህን ማድረጉ ላይ ዋና ተዋናይ የነበሩት ደግሞ ዛሬ ስለሃይማኖት እኩልነትና የእምት ነፃነት ተቆርቋሪ መስለው የተከፈተውን በር፤ የተከበረውን ነፃነት ለመዝጋትና ለማፈን እየታተሩ ስለመሆናቸው ከላይ በቀረበው ተጠየቅ መሰረት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ማስመሰል የደርጉ ባህሪ ነውና፡፡ ሌላም ያስመሰለው ነገር አለ፡፡ ደርግ የዘውዳዊ አገዛዙ የኢኮኖሚ ምንጭ የነበረውን መሬት በመንጠቅ የመሳፍንታዊ ሥርዓት መሰረት እንዲነቀል ያደረገ ቢሆንም ለገበሬዎች ያከፋፈለው መሬት ፍትሃዊነት የጎደለው የነበረ
ከመሆኑም ባሻገር አርሶአደሮች ምርታቸውን በገበያ ዋጋ እንዳይሸጡ የዋጋና የኮታ ቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት ሀብታቸውንና ዕውቀታቸውን አሟጠው በተሻለ ምርታማነት እንዳይሰሩና ኑሯቸውን እንዳይለውጡ ነፃነታቸውን ያፈነ ስርዓት በመሆኑም ማስመሰሉ ይገለፃል፡፡ ዛሬም ከመሬት መሸጥ መለወጥ ጋር ተያይዞ የሥርዓቱን ‹‹በኢህአዴግ መቃብር ላይ›› አቋም የሚያንኳስሱና ለህዝብ የቆሙ በማስመሰል የእነርሱን ምቾትና ጥቅም ያስጠበቀ የነበረ የኢኮኖሚ ስርዓት ለመመለስ እየተጋ መሆኑን ምናልባት አማራጭ ከተባለም የሚያቀርቡትን የፖሊሲ አማራጮች የሰማነውና የማንበቡ እድል የገጠመን ሁሉ ለማረጋገጥ አይከብደንም፡፡
በጥቅሉ
ከፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ ጋር ተያይዘው የሚነሱት ያለፉት ሁለት ስርዓቶች የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነታቸው የታፈነበት በሃገራቸው እንደሁለተኛ ዜጋ በመታየታቸው በሃገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ድምፅ ማሰማት የተነፈጉበት፣ ተሹመው በሚመጡ ባለስልጣናት እንጂ በራሳቸው ልጆችና ቋንቋ እንዲመሩ ያልቻሉበት፣ ኢትዮጵያ የብሄሮችና ብሄረሰቦች እስር ቤት የነበረችበት ዘመናት የነበሩ መሆኑ አያከራክርም፡፡
ስለሆነም
ነው የኢትዮጵያ ህብረብሄራዊ የፌደራል ስርዓት የተመሰረተበት አንዱና መሰረታዊ የሆነው መነሻ እነዚህ ስርዓቶች የፈጠሯቸውን የተዛቡ ግንኙነቶች ለማስተካከል ነው የሚባለው፡፡
የተዛቡ
ግንኙነቶችን በፌደራላዊ ስርዓቱ ማስተካከል ዋናው መነሻ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? የሚለውንም አጣመው የሚያቀርቡና ከሥርዓቱ እድሜ ማራዘም ጋር አያይዘው ለመሞገት የሚሹት ሃይሎች እንደቀደመው ሁሉ የተነጠቁትን ለማስመለስ በማስመሰል ደፋ ቀና የሚሉቱ ቢሆኑም የእነዚህን አስመሳዮች ጠባይ ለሚያውቁት ግን አላማቸው ማጣመም ነው ብሎ ከማለፍ በዘለለ ምን ማለት እንደሆነ በግልፅ መመልከት ተገቢ ነው፡፡
ያለፉት
ሥርዓቶች የፈጠሯቸውን ግንኙነቶች ማስተካከል ማለት የብሄሮች ብሄረሰቦችና የሃይማኖት እኩልነትን ማረጋገጥ ማለት ነው የሚለው የመጀመሪያው ትርጓሜ ነው፡፡ ይህ ሲብራራ እነዚህ ማንነቶች ቋንቋዎቻቸው፣ ባህሎቻቸው፣ ታሪኮቻቸውና ሌሎች የማንነት መገለጫዎቻቸውን እንዲያስፋፉና እንዲያሳድጉ የሚያስችላቸው እኩል እድል መፍጠር ማለት ነው፡፡ ያለፉት ስርዓቶች በህዝቦች መካከል የፈጠሩትን ጥርጣሬና መራራ በማስወገድ ኢትዮጵያ ሁሉም ማንነቶች እኩል የሚስተናገድባት የብሄር ብረሰቦችና ህዝቦች ቤት እንድትሆን በማድረግ በአይነቱ የተለየ እና አስፈላጊነቱ ጥርጣሬ ላይ የማይወድቅ ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ከታሪካቸው የወረሱትን በጎ ትስስር በማጎልበት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አዲስ የህዝቦች ግንኙነት መፍጠር ከፌደራላዊ ስርዓቱ መሰረታዊ አስተሳሰቦች ዋናው በመሆኑም ይህ አስተሳሰብ ከገዢ ስርዓቱ ግንዛቤን የማስጨበጥ እጥረትና ያለፉት ስርዓት ናፋቂዎች የእሩምታ ተኩሶች ተፅእኖ አንፃር የተፈለገውን ያህል ባይሆንም እስከነእጥረቱ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ መድረሱንና በፅኑ መሰረት ላይ መገንባቱን መካድ የማይችልና በውህደትና በመሬት ይሸጥ ይለወጥ እንዲሁም በኢትዮጵያዊነት ማስመሰያ ፕሮፖጋንዳዎች እንኳንስ ማስወገድ፤ ማነቃቃት የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱንም ከአዲስ አበባ ወጣ ብለው ይህንኑ በፅኑ መሰረት ላይ ገንብተው ተጠቃሚ የሆኑትን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብረሰቦችና ህዝቦች በመጠየቅና አኗኗራቸውን በመመልከት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ
ህብረ ብሄራዊ የፌደራል ስርዓት ልዩ ባህሪያት ከሚባሉትና በዋናነትም ከላይ እንደተገለፀው ያለፉና የተዛቡ ግንኙነቶችን ለማስተካከል የተደነገጉና የሃገሪቱን ተጨባጭ ህብረተሰባዊ መዋቅሮች የሚያንፀባርቁ ወይም የህብረ ብሄራዊ የፌደራል ሥርዓቱን አወቃቀር የሚወስኑ ጉዳዮች ማለት እንጂ ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት ኢትዮጵያን የመገነጣጠልና የመበተን ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ኢትዮጵያን ለመገነጣጠልና ለብተና ሊያበቁ የነበሩትን ስርዓቶች ደግሞ ፌደራሊዝምን ባላገናዘበ ውህደትና ፕሮፖጋንዳዎች አግባብ ለመመለስ የሚተጉ ሃይሎችን መመከትና ከማይቀለበስበት አለት ላይ መገንባት የሚያስችል አወቃቀሮችን የሚወስኑ ጉዳዮች ማለት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
የፌደራል
ስርዓቱ ልዩ ባህሪያት እንደሆኑ በህገ-መንግስታችን የተመለከቱ ነጥቦችም የመነጩበት የአስተሳሰብ ደርዝ የህዝብ ልእልናን ወይም የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ልዕልና መሰረት ያደረጉ ስለመሆናቸው ህገመንግስቱን ከነባራዊው ሁኔታ ጋር አገናዝቦ በማጤን በመገንዘብ ይቻላል፡፡ ከላይ እንደተገለፀውም የኢትዮጵያ ህዝቦች ባለፉት የዘውድና የደርጉ ስርዓቶች በሃገራቸው አንደ ሁለተኛ ዜጋ የተቆጠሩበት ፍፁም ፀረዴሞክራሲያዊ ስርዓቶችን ማሳለፋቸው እሙን ነው፡፡ የወቅቱ ገዢዎችና አገልጋዮቻቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ዕድል ለመወሰን የተቀመጡ አምባገነኖች እንጂ ህዝብን ሊያገልግ የተቀመጡ እንዳልነበረም ግልፅ ነው፡፡ ስለሆነም ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የሚጠበቀው አንዱና መሰረታዊ ጉዳይ የጥቂቶቹን ልዕልና ያሰፈነውን ያለፈውን ስርዓትና ለውርሱ የሚተጉ ሃይሎችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በማስወገድ የህዝቦችን ልዕልና ማረጋገጥ እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ሃገሪቱ የምትመራባቸው መሰረታዊ መርሆዎች፣ ፖሊሲዎችና ህጎች የሚመነጩት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፍላጎቶችን ለማሟላት ስለሆነ የመንግስት እንቅስቃሴዎችም ከዚህ አንፃር እንዲቃኙ ግድ ይላል ማለት ነው፡፡ ይህን ፈታ አድርገን ስንመለከተው የመንግስት ስልጣን፣ መንግስት የሚያራምዳቸው እምነቶች፣ የሚከተላቸው መርሆዎችና ፖሊሲዎች ምንጭ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ናቸው ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ የፌደራል ስርዓቱ ልዩ ባህሪያት፣ አወቃቀር ፣ የሥልጣን ክፍፍልና ትስስር መሰረታዊ መነሻ የህዝብ ልዕልና ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተቃዋሚዎቹ በፌደራላዊ ሥርዓቱ ላይ የሚለጥፉትንና በህዝብ ስም የሚደረጉትን የምርጫ ወቅቶች ግርግሮች በሚያጋልጥ መልኩ ከወረቀት ባለፈ በተግባር በተረጋገጡ ማሳያዎች የሚገለፅ ነው፡፡ ከእነዚህም ማሳያዎች ጥቂቶቹን ከተቃዋሚዎቹ ፀረ ፌደራላዊ አስተሳሰብና ግርግር አኳያ እያንሰላሰልን መመልከት ሃቁን ለመለየት እና እውነታውን ለመገንዘብ ያስችለናል፡፡
የመጀመሪያውና
የህዝብ ልዕልናን መስፈርት ላደረገው ፌደራላዊ ሥርዓቱ ሁነኛ ማሳያ የሚሆነው አሁን እያገለገለን ያለው የመንግስት መዋቅርና አወቃቀር በማንነቶች ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ በማንነቶች ላይ የተመሰረተ የመንግስት አወቃቀር ሲባል ምን ማለት ነው? ተጨባጭ መገለጫውስ ምንድነው? የሚለውን ስናይ፡ የኢትዮጵያ
ህዝቦች ባለፈውና ከላይ በተመለከተው አግባብ የተነፈጉትን ማንነቶችና መብቶች፣ ታፍኖ የነበረውን ታሪካቸውና፣ ቋንቋቸውን ባህላቸውንና ሌሎች የማንነት መገለጫዎችን በህገ-መንግስቱ ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን በተግባርም ተፈፃሚ ማድረግ እንዲቻል የፌደራል ስርዓቱ አባል መንግስታት የተደራጁት ወይም የተዋቀሩት በመሰረቱ በብሄር ብሄረሰብ ሆኗል፡፡
ይህ
የሆነበት ደግሞ ከላይ የተመለከቱት እንደተጠበቁ ሆነው ማንነቶች የተዛባውን ግንኙነት መወገዱን ማረጋገጫ እንደሆነ ስላመኑበትና በዚህ አወቃቀር አዲስ እኩልነት ግንኙነትና የጋራ ህልውና እንዲመሰረት ስለወሰኑ ነው፡፡
የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የግል መብቶችን ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደሆነ UN Human rights Committee ይገልፃል፡፡ ብዙ ፀሃፊዎች የቡድን መብቶች ከግል መብቶች ተለይተው መገደብ የሌለባቸው እንደሆኑ ይገልፃሉ፡፡ የግል መብትን በማረጋገጥ ብቻ የቡድን መብቶችን ማረጋገጥ እንደማይችል፣ የቡድን መብቶችን የሚከለክል ስርዓት ሊሆን እንደማይችል ይጠቅሳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ያደጉ የዴሞክራሲ ሀገሮች የቡድን መብቶችን በተሟላ መልኩ ባለማረጋገጣቸው ምክንያት የቡድን መብት ጥያቄዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከሩ የሃገሪቱን ውስጣዊ ሰላም በማናጋት ላይ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያን
ሁኔታ ስንመለከት የብሄር፣ ብሄረሰቦች እስር ቤት ልትሆን የቻለችው የቡድን ማንነቶች ማፈን ዋነኛ የጭቆና መገለጫ ስለነበር ነው፡፡ ይህን ጭቆና በትግል በማስወገድ የራስ አስተዳደር መብትን በማረጋገጥ ብቻ የሚመለስ አልነበረም፡፡ ህገ መንግስቱን በማፅደቅ ሂደት ሲነሱ የነበሩ ጥያቄዎችና ክርክሮች ይህንን ግልፅ ያደርጋሉ፡፡ የአንዳንድ ብሄሮች የፖለቲካ ድርጅቶች ከጅምሩ የመገንጠል ጥያቄ አንስተዋል፣ አንዳንዶች ደግሞ ነባሩ የተዛባ ግንኙነት በፈጠረባቸው ስነ ልቦናዊ ጫና ምክንያት በሰንደቅ ዓላማ ቀለማት አመራረጥ ሳይቀር በስፋት መከራከራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ከመገንጠል በመለስ ያለውን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ማረጋገጥ ለብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በእርግጥ የሚያረካ እንዳልነበረ ነው፡፡ ካለፉት 24 ዓመታት ተጨባጭ ተሞክሮ የምንረዳው ጉዳይ የመገንጠል መብት የብሄርና ተጓዳኝ ጭቆናዎች ለማስወገድ ዋስትና ተደርጎ እንደታየ፣ እንዲሁም ይህ መብት በህገ መንግስት ከተደነገገ በኋላ ጥያቄውን ሲያነሱ የነበሩ ሃይሎች በህብረቱ መቀጠል መቻላቸውን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ስርዓት አንዱና ልዩ ባህሪው የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት በማረጋገጥ ህብረትን ማስቀጠል መቻሉን የሚያመላክት እንጂ ለብተና የሚያበቃ አይደለም ፤ አይሆንምም፡፡
ህዝብና
መንግስት በጋራ ባደረጉት ጥረት ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት የተመዘገበ መሆኑ ቢታወቅም ድህነት አሁንም ዋና ፈተናችን እንደሆነ ቀጥሏል።
በመጀመሪያው
የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ህዝብና መንግስት ቀን ከሌት ከደከሙበት አንጻር ሲመዘን ውጤቱ ከዚህም በላይ ሊሄድ ይችል እንደነበር ከማንም የተሰወረ አይደለም። የማስፈጸም አቅም ማነስ የፈጠረው ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራት የፈጠሩትን ዕንቅፋት መሻገር ራሱን የቻለ ጊዜና ጥረት ጠይቋል፡፡ በመልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል የታዩትን ችግሮች በመጠቀም ጭምር ኪራይ ሰብሳቢዎች ለግል ጥቅማቸው የምትመች ደሀና ደካማ ሀገር ለመፍጠር አጀንዳዎቻቸውን እየቀያየሩ ሲሰሩ የቆዩና አሁንም ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነትን በጠባብ ብሄርተኝነትና ትምክህት እየበረዙ መሆኑም ከላይ በተመለከተው አግባብ ይታወቃል፡፡ የግል ጥቅም ለማጋበስ አሰራሮችን እስከማዛባትና ሙስናን እስከማስፋፋት መሄዳቸውም በተመሳሳይ። እነኚህ ኃይሎች አሁንም በህዝብና በመንግስት ዕቅድና ተግባራዊ ጥረት ላይ ተጨማሪ ፈተና ሆነው እየቀጠሉ ይገኛሉ፡፡ ዋና ጠላታችን ድህነትን ባሰብነው ጊዜ አሸንፈን መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገርና ህዝብ ለመፍጠር ያለንን ራዕይ የሚያደበዝዙ የተስፋችንና የውጤታችን ሳንካዎች ሆነዋል።
ስለሆነም
ህዝብና መንግስት ከፀረ ድህነት ትግሉ ጎን ለጎን ኪራይ ሰብሳቢነትንና እርሱ የፈጠራቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመድፈቅ የጋራ አቋም ላይ ደርሰዋል። ከዚህም ተነስተው ይህን ዕንቅፋት ከውስጥም ከውጭም በመለየት ከወትሮው በጠነከረ መልኩ ለመፋለም በተቀናጀ መልኩ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ። እንደተለመደውና በሰሞኑ እንዳየነውም ይህ የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት የተቀናጀ ትግል የሚጎዳቸው አካላት የተለያየ ምክንያት በመፍጠር ትግሉን ለማስቆም ከየትም ተጠራርተው በመሰባሰብ የሞት የሽረት ጥረት እንደሚያደርጉ በገሃድ ታይቷል፡፡ በቀጣይም ሙከራቸውን ያቋርጣሉ ተብሎ አይጠበቅም። በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በየራሳቸው ምክንያት የሀገራችንን ዕድገት የሚጠሉ አካላት እየተቀናጁ የልማት መንገዳችንን ለማስተጓጎል እየተራወጡ መሆኑንም መዘንጋት አይገባም። የፌደራል ስርዓታችን፣ የዴሞክራሲና የኢኮኖሚ ግንባታችን እየሰመረ መሄድ የተዳከመች ወይም የተከፋፈለች ኢትዮጵያን በመፍጠር የግል አጀንዳቸውን ማሳካት ለሚፈልጉ ኃይሎች የራስምታት ነው።
የኢትዮጵያ
ህዝቦችና የኢፌዴሪ መንግስት በዚህ ወሳኝ ወቅት አጀንዳቸው አንድና አንድ ብቻ ነው… ድህነትን ለማሸነፍ የተጀመረውን ጉዞ በማስቀጠል የበለፀገ ህዝብና ሀገር መፍጠር።
ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አስተማማኝ የኢኮኖሚ ዕድገትና ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበት ነው። ከዚህ ጋርም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን በበለፀገ የህብረተሰብ አስተሳሰብና በዘመነ አሰራር ፤እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነትን በማጎልበት ጠባብ ብሄርተኝነትን መድፈቅ የሚያስችለን ነው። የአገልግሎት አሰጣጥ የመልካም አስተዳደር ችግርንም ዘላቂ በሆኑ አሰራሮች የምንፈታበት ዕቅድ ነው። በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ የዜጎቻችንን ክብር ከፍ የምናደርግበት፣ የመደመጥ አቅማችንን ጭምር የምናሳድግበት ነው። የመልካም አስተዳደር ችግርን ጨምሮ ድህነት የፈጠራቸው ማህበራዊ ሳንካዎችን ሁሉ መሰረታዊ በሆነ መልኩ በማሸነፍ በየዕለቱ በሚደመሩ ድሎች ታጅበን እየገሰገስን ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማሳካት ብቸኛ አማራጫችን ነው፡፡
No comments:
Post a Comment