መቃብሽ ርግበይ

***
የትልቅና የታላቋ አገር ቻይና ዋና የፖለቲካ ማእከል ቤይጂንግ የመንግስት ብቻም ሳትሆን የኮሚኒስት ፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ ምክር ቤት ፅ/ቤት መገኛም ነች፡፡
ኮሚኒስት ፓርቲ ቻይና የተወለደው በ1921 እ.ኤ.አ ነበር፡፡ ቻይና ለሶስት አስርት አመታት በርስበርስ ጦርነትና ራሷን ከጃፓን ወራሪ ሃይል ጋር ጦርነት ላይ ያሳለፈች ሃገር ናት፡፡ ኮሚኒስት ፓርቲው በ1949 የኮሚታንት መንግስትን ከቻይና ዋና ክፍል አስወግዶ መንግስትነት ተቆጣጠረ፡፡ ህዝባዊት ሪፓብሊክ ቻይና መሰረተ፡፡ አብዮቱን በመምራትና ሪፓብሊክ ቻይና በመመስረት ማኦ ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡ ነገር ግን በህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ ምስረታ ማኦ ፤ ‹‹ቻይና ደካማ ኢንዳስትሪ ነው ያላት፡፡ ገንዘብዋ ትርጉም የለውም፡፡ በከተሞች ስራጥነት ተንሰራፍቷል፣በገጠር የሰብል እጥረት ገጥሟል፡፡ በአንፃሩ የቻይና ህዝብ በአመት በ14 ሚሊዮን እየጨመረ ነው፡፡›› በማለት ያደረገው ታሪካዊ ንግግር ሃገሪቷ በምን ያህል ቀውስ ውስጥ እንደነበረች ያሳያል፡፡
ቻይናውያን ማኦ
በሚያቀነቅነው ‹‹አዲስ ዴሞክራሲ›› ፅንሰ ሐሳብ ከሩሲያ የተለየ የሶሻሊዝም ኮሚኒዝም አተያይ እንዳላቸው
አስቀመጡ፡፡ አንዳንዶቹ ማኦይዝም ይሉታል፡፡ ይህንን ተከትሎ በ1950 የግብርና ሪፎርም ህግ ይፋ ተደረገ፡፡
በ1956 ደግሞ የግብርና ስርአቱ ወደ ወል እርሻ እንዲሆን ተደረገ፡፡ ይህንን ተከትሎም በሚሊዮን የፓርቲው አባላት
የሪፎርም መፅሐፍ ይዘው፣ የሚያደሉት የግብርና እንስሳት፣ማሽነሪዎች አስከትለው ገጠር ገቡ፡፡ አርሶ አደሩም መሬት
እንዲያግኝ ተደረገ፡፡ በ1953 የግል ኢንዳስትሪና ቢዝነስ በሙሉ በማገር ሶሻሊስት ኢኮኖሚ እንደሚገነባ ይፋ
ሆነ፡፡በተመሳሳይ አመትም የጋብቻ ህግ ወጣ፡፡ በእነዚህ ስር ነቀል እርምጃዎች በእርግጥም በመጀመሪያ አመታት
በኢኮኖሚው እምርታ የሚመስል እድገት ተመዘገበ፡፡ በ1952 የቻይና ኢኮኖሚ በ1936 ከነበረው በእጥፍ አደገ፡፡
የኢኮኖሚ ግሽበቱ ተገታ፡፡ የአርሶአደሮችና ላባደሮች ጤና እና ኑሮ መሻሻል አሳየ፡፡ ነገር ግን የለውጥ ብርሃኑ
የአደጋ ደመና አንዣበበት፡፡ በ1958 ማኦ ‹‹ታላቅ እመርታ ወደፊት›› የሚል ፖሊሲ ይዞ መጣ፡፡ ይህ ከተማውም
ገጠሩም፣ ኢንዳስትሪውም ግብርናውም ያተራመሰ ‹‹በሁለት ጉልበታቸን እንራመድ›› በሚል መፈክር የተቀነቀነው የማኦ
የስህተት መንገድ ግን መስፈንጠር ቀርቶ መዳኽ የጀመረው የቻይና ኢኮኖሚን እንደ ሙቀጫ እንዲንከባለል አደረገው፡፡
‹‹እመርታው›› ትልቅ ርሃብን አመጣ፡፡ ከ1958 እስከ 1961 በተከታተለው ታላቁ ረሃብም ከ20 ሚሊዮን በላይ
ቻይናውያን እንደቅጠል ረገፉ፡፡ የህዝባዊት ሪፓብሊክ ቻይና የመጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበረው ዝሁዋ
ኢናሊያ/Zhou Enlai/ የአስቸኳይ አደጋ ፕሮግራም እንዲቀረፅና እንዲተገበር ማኦን ቢጠይቅም ተሰሚት አላገኘም፡፡
ማኦ፤ በአንፃሩ ለ10 አመት የቆየው /1966 እስከ 1976/ ታላቁ የላባደር ባህላዊ አብዮት አወጀ፡፡ ፕሮግራሙ ከኢኮኖሚ እድገት ይልቅ ፖለቲካዊ ትርምስ የበዛበት ሆነ፡፡ የቻይና ኢኮኖሚ ከድጡ ወደ ማጡ ተንከባለለ፡፡ በፓርቲው ውስጥ ፅንፈኛ ግራና መሃል ግራ በሚል ክፍፍል በተፈጠረው ትርምስና ማኦ ራሱ ያበረታታው ‹‹ማዘዣው ጣቢያው ባዳፍኔ ደብድብ››/Bombard the Headquarter/ የሚለው የውስጥ ፓርቲ ትርምስ የፓርቲው ሰዎቸ እርስበራሳቸው ተላለቁ፡፡ የማኦ ባለቤት በመራችው ‹‹በአራቱ ጋንግ›› የሚመራው የፅንፈኞች እርምጃ መጨረሻው ማኦም የማይቆጣጠረውና ለሱም ወደማይመለስ ደረጃ ደርሶ ነበር፡፡ በዚህ ትርምስ መካከል ግን በ1976 ማኦ ከዚህ አለም በተፈጥሮ ሞት ተለየ፡፡ በእግሩ የተተካው ደንግ ዞኣፒንግ የቻይና ባህላዊ አብዮት ማብቃቱ አስነገረ፡፡ በምትኩ ‹‹ቻይናዊ ሶሻሊዝምን›› አወጀ፡፡ ቻይና ገበያመር ኢኮኖሚ እንደምትከተልም አሳወቀ፡፡ በሚከተለው የሪፎርምና ክፉትነት ፖሊሲም ከምዕራባውያን ግንኝነት መሰረተ፡፡ የውጪ ኢንቨስተሮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተፈቀደ፡፡ የ‹‹አራት ዘመናዊነት›› ፕሮግራም ማለትም በግብርና፣ኢንደስትሪ፣ ሳይንስና ቴክሎጂ እና በወታደራዊ መስክ ቀረፀ፡፡/የታሪክ ተማራማሪዎች ግን ቀደም ሲል በዝሁዋ ኢናሊያ ተዘጋጅቶ የነበረ ነው ይላሉ፡፡/
የሆኖ ሆኖ በዶንግ ፖለሲም ቻይናን ፈጥኖ አልተደረጋጋችም፡፡ የተማሪዎቸ የታንክ ጭፍጨፋን ጨምሮ ቻይና ብዙ ዋጋ ካስከፈላት በኋላ ተደጋጋሚ በተደረገ የኢኮኖሚ ሪፎርም ኢኮኖሚው አንሰራራ፡፡ በ1992 ቻይና “socialist market economy” የመገንባት ግብ የሃገሪቱና የፓርቲው ግብ መሆኑ በ14ኛው ፓርቲው ጉባኤ ይፋ አደረገ፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ የቻይና ጉዞ የስኬት ጉዞ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ይህ ፖለቲካው ሶሻሊዝም ኢኮኖሚው ሶሽዮ ካፒታሊዝም ቅርፅ የያዘ የቻይና እድገት ቤይጂንግ ላይ በከተሙት ግዙፍ የፓርቲ ተቋማት ይመራል፡፡ በእርግጥ በቻይና በመንግስትና በድርጅት መካከል ያለው መለያ መስመር ለራሳቸው ካልሆነ ለሌላው በቀላሉ የሚገባ እንዳልሆነ በቆይታዬ ተረድቻለሁኝ፡፡ ለእነሱ ጠቅሟቸዋል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በማንም ሃገር ኮፕ ፔስት ቢደረግ ግን የሚመረጥ አዋጪ መንገድ ይሆናል ብዬ አላስብም፡፡ ምክንያቱ ሃገራት የየራሳቸው ታሪካዊ፣ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚየዊ፣ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ልዩነት አላቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ ለስርአተ መንግስት ቀረፃ መሰረታዊ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንም ከቻይናውያን ስህተትና ስኬት የምንወስደው ተሞክሮ እንዳለ ሁሉ የምንጥለውም ብዙ ነገር አለ፡፡/የተጠቀምኩበት አቆጣጠር በሙሉ እ ኤ አ ነው/

No comments:
Post a Comment