በቀደሙት አጠቃላይ ምርጫዎች ኢህአዴግ በህዝባችን ይሁንታ በአብላጫ ድምፅ እያሸነፈ ከህዝቡ የተሰጠው ከፍተኛ ኃላፊነት በቁርጠኝነትና በከፍተኛ ዲስፕሊን እየተወጣ መጥቷል። በምርጫ 2002 ደግሞ የሀገራችን ተቃዋሚዎች ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከምክር ቤቶች የተገለሉበት ሁኔታ ሲፈጠር ኢህአዴግ ደግሞ በአንፃሩ ከፍተኛ ይሁንታን አግኝቷል። ከህዝቡ የተሰጠው ከፍተኛ ኃላፊነት በመገንዘብም የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱን ይበልጥ ለማጎልበት የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎች አከናውኗል። ኢህአዴግ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ለማጠናከር በቁርጠኝነት ሲሰራ የሀገራችን ተቃዋሚዎች ግን ህዝቡን ሊያሳምን የሚችል የፖሊሲ አማራጭ ማቅረብ ባለመቻላቸው የሀገራችን ህዝቦች ይሁንታ በተደጋጋሚ ተነፍገዋል፡፡ በመሆኑም ኢሕአዴግ የአውራ ፓርቲ መልክ ይዞ እንዲጓዝ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
የሀገራችን ህዝቦች የሀገሪቱን ህዳሴ እውን ለማድረግ በከፍተኛ ቁርጠኝነት ሌት ተቀን ለሚተጋው ኢህአዴግ ድምፃቸው
ሰጥተው ተቃዋሚዎች ግን የሀገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ማረጋገጥ እንደማይችሉ በድምፀቸው ባረጋገጡበት ሁኔታ
ተቃዋሚዎች የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ የተቀለበሰ ለማስመሰል ተረባርበዋል፡፡ ህዝቡ ለምን ድምፁን እንዳልሰጣቸው
ራሳቸውን በአግባቡ ፈትሸው ለማሻሻል ከመሯሯጥ ይልቅ ኢህአዴግን መኮነን መርጠዋል። የአውራ ፓርቲ ስርዓትን ከአንድ
ፓርቲ ስርዓት ጋር ለማመሳሰልና መሰረተ ቢስ በሆነ ክስ ህዝቡን ለማደናገርም ሞክረዋል፡፡
የአውራ ፓርቲ ስርዓት በተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች ተግባራዊ የሆነና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት አካል ሆኖ ሳለም ኢህአዴግ ያመጣው እስከማስመሰል ተጣድፈዋል። በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት በተሻለ ሁኔታ ተራምደዋል የሚባሉ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ሳይቀር የአውራ ፓርቲ ስርዓት እውን ሆኖባቸዋል። የሲዊድን ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ የሜክሲኮው ሪቮልሽናል ኢንስቲትሹናል ፓርቲ እንዲሁም የጃፓኑ ሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ከ40 እስከ 60 ዓመታት በስልጣን የቆዩበት እውነታ እናገኛለን። በአህጉራችን አፍሪካም የአውራ ፓርቲ ስርዓት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየና አሁንም ያለ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት አንድ አካል ነው፡፡
በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ወሳኙ ጉዳይም የትኛው ፓርቲ ስንት ጊዜ በስልጣን ላይ ቆየ ሳይሆን ህዝቡ በእውን ድምፁን በነፃነት ይሁንታውን ሰጥተዋል ወይ የሚለው ይሆናል። እናም ህዝቡ በነፃነት ወጥቶ ያለምንም ጫናና ተፅዕኖ ድምፁን እስከሰጠና የመንግስታዊ ስልጣን ብቸኛው ምንጭ ህዝቡ እስከሆነ ድረስ የህዝቡ ይሁንታ ያገኘ አካል በተደጋጋሚ መመረጡ ስርዓቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት አይደለም ተብሎ ከተቃዋሚዎች የሚነሳው ሐሳብ ውሃ የሚቋጥር አይደለም።

No comments:
Post a Comment